​አካላቸው የተለያየ ቢሆንም በዋነኛነት ግን ቀላ ያለ ቡናማ ቀለም ያላቸው ትላልቅ  አዳኝ ወፎች ናቸው፡፡

​የአፍሪካ ጎሽ ሊጎዳው የሞከረንና  የጎዳውን ሰው ከዓመት በኋላም ቢሆን የማስታወስ ችሎታ አለው፡፡ ይቅርታ የማድረግ ባህሪ ስለሌለውም ባገኘው አጋጣሚ የጎዳውን ሰው ካገኘ ብድሩን ይመልሳል፡፡ 

​‹‹አዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› ሾለቅን አፈ ሹል አሞራ ይለዋል፡፡ እሱ ሲጮህ  ዝናም ይመጣል ይባላል፡፡ 

​ድኩላ ዝርያው ከአጋዘን ወይም ኒያላ ይመደባል፡፡ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች የሚገኘው ድኩላ፣ በኢትዮጵያ አንዳንድ ስፍራዎች ለምግብነት ያገለግላል፡፡

ሽኮኮ ፅድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅምና ፀጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል።

ድብ ከአጥቢ እንስሳት ይመደባል፡፡ ድቦች በዋነኛነት የሚመገቡት ፍራፍሬና አትክልቶችን ነው፡፡ አንዳንዴ በጐችን እንደሚበሉም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ድመትን የቤት አውሬ፣ ለማዳ የሚሏት አሉ፡፡ ዓይኗ ልዩ በመሆኑም ድብርቅ ዓይን፣ ያይጥ ጠላት የሚላት መዝገበ ቃላቱ፣

Pages