ከአንድ ሳምንት በላይ ሲካሄድ የቆየው የለንደኑ 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ (ነሐሴ 7 ቀን 2009 ዓ.ም.) ይጠናቀቃል፡፡ ኢትዮጵያ እስከ ዓርብ ምሽት (ነሐሴ 5 ቀን) ድረስ በነበራት ደረጃ በ1 ወርቅና 2 ብር አምስተኛውን ስፍራ ይዛለች፡፡ 

የአፍሪካ  እግር  ኳስ  ኮንፌዴሬሽን  (ካፍ) ከሳምንታት  በፊት  ለአፍሪካ እግር  ኳስ  ማደግ  አስተዋፅኦ  ያደርጋል  ያለውን  አዲስ  የውድድር  መርሐ  ግብርና  የተሳታፊውን  ቁጥር  ከ16  ወደ  24  ከፍ  ማድረጉ  ይታወሳል፡፡ 

በኬንያ ለሚስተናገደው የ2018 የአፍሪካ አገሮች የእግር ኳስ ሻምፒዮና (ቻን) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የአቋም መለኪያ ጨዋታውን ከዛምቢያ ጋር ያደርጋል፡፡  

የሁለት ቀናት ዕድሜ የቀረው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዳዲስ ክስተቶችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተለይ ከዓለም ድንቅ አትሌቶች መካከል ጃማይካዊው ዩሴን ቦልት የውድድር ዘመኑ ማጠናቀቂያና የ5,000 እና 10,000 ሜትር ተፎካካሪው ሞ ፋራ የመሞ የሩጫ መቋጫ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ከሳምንት ያነሰ ዕድሜ የቀረው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በለንደን ከተማ ይካሄዳል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኖቹን ባለወርቆች ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

Pages