አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!
አዲሱን ድረ ገጽ ይሞክሩ!

የሁለት ቀናት ዕድሜ የቀረው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አዳዲስ ክስተቶችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በተለይ ከዓለም ድንቅ አትሌቶች መካከል ጃማይካዊው ዩሴን ቦልት የውድድር ዘመኑ ማጠናቀቂያና የ5,000 እና 10,000 ሜትር ተፎካካሪው ሞ ፋራ የመሞ የሩጫ መቋጫ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

ከሳምንት ያነሰ ዕድሜ የቀረው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በለንደን ከተማ ይካሄዳል፡፡ የኦሊምፒክና የዓለም ሻምፒዮኖቹን ባለወርቆች ጨምሮ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አትሌቶች ከፍተኛ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡  

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሐምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ጫላ ቢዮ በአሠልጣኙ ዮሐንስ መሐመድ ላይ በፈጸመው ድብደባ ከማንኛውም ውድድር ሁለት ዓመት እንዲታገድ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ከአዲሱ ሩብ በጀት ዓመት በኋላ እንደሚካሄድ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤ፣ ላለፉት አራት ዓመታት የቆየውን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራር ለማሰናበት ወይም እንዲቀጥል የሚያደርገውን አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫም እንደሚያካሂድ ይጠበቃል፡፡

  • ቀነኒሳ በቀለ በሕመም ከቡድኑ ራሱን አግልሏል

  የኢትዮጵያ አትሌቲክ ፌዴሬሽን ከሐምሌ 28 ቀን እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ በእንግሊዝ ለንደን በሚስተናገደው 16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚወዳደሩ ብሔራዊ አትሌቶችን ዝርዝር ይፋ አደረገ፡፡

በኢትዮጵያ ከሚዘወተሩና የተመልካችን ቀልብ መሳብ ከሚችሉ ስፖርቶች  አንዱ የእጅ ኳስ ነው፡፡ ከእግር ኳስና አትሌቲክስ ባሻገር በኅብረተሰቡ የሚዘወተረው የእጅ ኳስ የራሱን ፌዴሬሽን በማቋቋም የተለያዩ ውድድሮች ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ 

የስፖርቱ አደባባይ የጅረት መቧደኛ እየሆነ መምጣቱ ሳያንስ መቃቃርን የሚፈጥር የኳስ ሜዳ እንኪያ ሰላንቲያ ማስተናገጃ የመሆኑ ነገር አሳሳቢ መሆኑ ብቻም ሳይሆን፣ የዚህ ሁሉ ምክንያቱ አመራሩና የመንግሥት አካል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ 

ኬንያ ያስተናገደችው አሥረኛው ከ18 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሐምሌ 5 እስከ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ ተካሂዶ ባለፈው እሑድ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡

Pages