የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽንና በአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ስፖርት ቁልፍ ቦታ ያለው ናሽናል ባስኬት ቦል አሶሴሽን (ኤንቢኤ) በጋራ ለመሥራት ተስማሙ፡፡ ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተነግሯል፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ጋቦን ያስተናገደችው 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በካሜሮን የበላይነት ባለፈው እሑድ ጥር 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ ዘጠኝ ጊዜ ለፍጻሜ የበቃችው ግብፅ በጨዋታው ግብ የማስቆጠሩን ቅድሚያ ብትወስድም ውጤቱን ማስጠበቅ ተስኗት ዋንጫውን አሳልፋ ሰጥታለች፡፡

ከ1975 ዓ.ም. ጀምሮ የስፖርት ማኅበር በማቋቋም ላለፉት 34 ዓመታት በስፖርት ውስጥ ሲወዳደር የቆየው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት (ኢመድ)፣ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ማክሰኞ ጥር 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ለግንባታው የሚያስችለውን የመሠረት ድንጋይ አኑሯል፡፡

-   አይኦሲ ‹‹ንፁህ አትሌቶችን እንጠብቅ›› የሚል አዲስ ዘመቻ  ጀመረ 

 በአገር ደረጃ በቅርቡ የተቋቋመው ብሔራዊ የፀረ ዶፒንግ ጽሕፈት ቤት ሕግ በየካቲት ወር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ 

በቅርቡ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ቀን ተቆርጦለት ሲጠበቅ የነበረው የዓለም አቀፍ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) የዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ እንደማይካሄድ ድንገት ሲታወቅ ግራ ከማጋባት አልፎ አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

-  የኢትዮጵያ የለንደን ኦሊምፒክ ደረጃ 22ኛ ሆነ

ዓመት በፊት በለንደን በተዘጋጀው 30ኛ ኦሊምፒያድ በ3,000 ሜትር መሰናክል የነሐስ ሜዳለያ ያገኘችው ኢትዮጵያዊቷ ሶፍያ አሰፋ፣ ሜዳሊያዋ ወደ ብር ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

Pages