በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤኣይዲ)፣ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሁም ዱፖንት በተባለው የአሜሪካ ኩባንያ ትብብር በተሻሻለ የበቆሎ ዝርያ ፕሮግራም አማካይነት ተጠቃሚ የሆኑ 250 ሺሕ ገበሬዎች፣ በሔክታር 7.5 ሜትሪክ ቶን ምርት መሰብሰብ እንደቻሉ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

የአገሪቱ የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኮች ለውድድሩ ዕጩ መሆን ባልቻሉበት የዓመቱ የአፍሪካ ባንኮች ሽልማት መስክ፣ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ በፋይናንስ መስክ ዕጩ መሆኑ ታወቀ፡፡

በፖታሽ ማዕድን ኢንቨስትመንት ዘርፍ ውስጥ ለመሰማራት አላና ፖታሽ ከተባለው ኩባንያ ሙሉ አክሲዮኖችን በመግዛት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው የእሥራኤሉን አይሲኤል ኩባንያ፣ የፓታሽ ማምረቻ ይዞታውንና ንብረቱን መንግሥት ተረከበ፡፡

የአዲስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ በዓመት ሦስት ጊዜ በቋሚነት ከሚያዘጋጃቸው የንግድ ትርዒቶች አንዱ የሆነው ‹‹አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ ልዩ የግብርና እና የምግብ ንግድ ትርዒት›› ከ75 በላይ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ተገለጸ፡፡ 

  • ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ አስመዘገበ

የአገሪቱን የቢራ ገበያ ከተቀላቀለ አንድ ዓመት ከዘጠኝ ወራት ያስቆጠረው ሐበሻ ቢራ አክሲዮን ማኅበር ካፒታሉን ለማሳደግ በተጠራው ስብሰባ ወቅት፣ ባለአክሲዮኖች የድርጅቱ ካፒታል ወደ 2.2 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል መወሰናቸው ተገለጸ፡፡ 

  • የዓለም ባንክ የንግድ አሠራር መለኪዎችን ለማሻሻል ሩዋንዳ ሞዴል ተደርጋለች

ካቻምና በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊን ለመዘከር የሩዋንዳ መንግሥት በመሠረተው ፋውንዴሽን ሲምፖዚየም ላይ ለመታደም ቢሆንም ከሰሞኑ ግን በ11 መስኮች ላይ የተደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ለመፈራረም ነበር ወደ ኪጋሊ ያቀኑት፡፡

  • የኢትዮጵያ የዘርፍ ምክር ቤት ምርጫ ቀን ተቆርጦለታል

 

ከስምንት ወራት በላይ ሲያወዛግብ ከመቆየቱም ባሻገር ለአገር አቀፉ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔ መዘግየት ምክንያት እንደሆነ ሲጠቀስ የቆየው የአማራ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፈርሶ እንደ አዲስ ተመሠረተ፡፡

Pages