- ከውጭ የሚገባውን 90 ሺሕ ቶን የገበታ ጨው ያስቀራል ተብሏል

በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ በ500 ሚሊዮን ብር ወጪ የጨው ፋብሪካ ሊቋቋም ነው፡፡ ለፋብሪካው ግንባታ ሐሙስ ታኅሳስ 21ቀን 2009ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስምንተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ ችግር እንዳጋጠመው በመግለጹ ምክንያት ችግሩን ለመፍታትና ተፈጠሩ የተባሉትን አለመግባባቶች ለመቅረፍ የተቋቋመው አጣሪ ግብረ ኃይል ሪፖርቱን ይፋ አደረገ፡፡ 

​የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ የሚያስችሉ ችግሮች ገጥሞኛል በማለት በሥሩ የሚገኙትን  18ቱን አባል ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች በመጥራት ማወያየቱና መፍትሔ ይሆናል ብሎ ያመነበትን ውሳኔ ያስተላለፈው ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ 

​ኢትዮጵያዊ ስያሜ ያለውና ከመነሻውም በኢትዮጵያ መገኘቱ የሚታመነው ጎመን ዘር፣ በሳይሳዊ አጠራሩ ብራሲካ ካሪናታ፣ አቢሲኒያን ሬፕ፣ አቢሲኒያን ሙስታርድ አለያም ኢትዮጵያም ሙስታርድ እንደሚባል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Pages