​እነሆ መንገድ። ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ ድልድይ ልንጓዝ ተሳፍረናል። ሰው በሰው ላይ እንደጥልፍ ጥለት ተደራርቦ ይተፋፈጋል። ቅብጥብጡ ወያላ፣ ‹‹አንድ ሰው አንድ ሰው…›› እያለ ሲጮህ ዕቃ እንጂ ሰው የሚጭን አይመስለውም። 

እነሆ ጉዞ ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ። ምድር ትውልድን በትውልድ እየተካች የደከመውን በሞት ሸኝታ ለጋውን እያሳደገች ፋታ አሳጥታ ታራውጠናለች።

​እነሆ መንገድ። ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ልንጓዝ ነው። ይኼኛው መንገድ ከትናንትናው በአባት አይገናኝ እንጂ በእናት አንድ ነው። ድልድያቸው ሕይወት ትባላለች። 

እነሆ መንገድ! ከሜክሲኮ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ጎዳናው በባለርስቶቹ ዘመን ብዙ ለምዶ ኖሮ እንደተወረሰ ሰፊ እልፍኝ፣ ‹አቤት አቤት አልኩኝ ብቻዬን ቀርቼ. . .› ይባልበት ይዟል። እልፍ ነን።

እነሆ ዛሬ የምንጓዘው ከቦሌ ወደ ካዛንቺስ ነው። ሁሉም ሠፈር አቋራጭ እንጂ አገር አቋራጭ ባለመሆኑ ከአንድ ራሱ በቀር ተጎታች ሳይኖረው ይሳፈራል። ወያላው ራቅ ብሎ ቆሟል። 

​እነሆ መንገድ! ከሽሮሜዳ ወደ ላይ ወደ እንጦጦ ልንወጣ ነው። ታክሲያችን ውይይት የምትባለዋ ናት። የመንገደኛው ብዛት በአካባቢው አገልግሎት ከሚሰጡ ታክሲዎች ጋር ስለማይመጣጠን፣ ወያላው ጥርሱን እየፋቀ እጁን ኪሱ ከትቶ በወጭና ወራጁ ይደበራል።

​እነሆ ዛሬ የምንጓዘው ከመገናኛ ወደ ቦሌ ነው። ሁሉም ሠፈር አቋራጭ እንጂ አገር አቋራጭ ባለመሆኑ ከአንድ ራሱ በቀር ተጎታች ሳይኖረው ይሳፈራል።

​እነሆ ጉዞ! እነሆ መንገድ! ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። የተሳፈርንበት ‘ሃይገር ባስ’ በመንገደኞች ታጭቋል። መስኮቶች ተከፋፍተዋል። በተከፈቱት መስኮቶች እየነፈሰ የሚገባው አየር ግን የተዘጋ ነው። 

Pages