​እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ ስድስት ኪሎ። የጎዳናው ጭብጥ ተደጋጋሚ ነው። ሕይወት ቀለም ያለቀባት ትመስላለች። በመንጋ ቅርፅ አሠልፋ የምትነዳው እልፍ ነው።

​እነሆ መንገድ። ከመርካቶ ወደ ፒያሳ ልንጓዝ ተሳፍረናል። የአዳም ዘሮች በአቤልና በቃየል ጎራ ተከፍለው በዚህች ቋት በሌላት ዓለም ውስጥ ዛሬም መንገዱን አጣበውታል። 

​እነሆ መንገድ ከኮተቤ ወደ ቀራኒዮ። ‹‹የሴት ልጅ ሸክሟ በእንስራ ውኃ ነው፣ አንቺን የደም ገንቦ ያሸከመሽ ማን ነው?›› እያለ ወያላችን አጠገቤ የተቀመጠችውን አንገተ ብርሌ ያደንቃል። 

​እነሆ መንገድ። ከአያት ወደ ጦር ኃይሎች። ያጠበቁት እየላላ፣ ያላሉት እየጠበቀ፣ በፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ግራ መጋባት የሄድንበትን መንገድ ደግመን ልንሄድበት ባቡር ተሳፍረናል። 

​እነሆ መንገድ። ከሳሪስ አቦ ወደ ቦሌ ድልድይ ልንጓዝ ነው። ዙሪያ ገባውን በጨረፍታ ስንቃኘው በአቧራ ሸማ የወየበው ዓይናችን እርስ በርሱ ይጋጫል።

በሥራም ሆነ በትምህርት ምክንያት በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ታክሲ ውስጥ ገባ ብሎ መውረድ አይቀርም፡፡

Pages