ኅብረተሰቡን በማሳተፍ፣ መረጃ በመለዋወጥና በቅርበት ነገሮችን በጋራ በመከታተል የፍትሕ ሥርዓቱን ማስጠበቅና የሕግ የበላይነትን ማስከበር ካልተቻለ በስተቀር፣ በየመንገዱና በየሠፈሩ ጠብመንጃ ይዞ በመቆም ብቻ ወንጀልን መከላከል እንደማይቻል የፌዴራል የፍትሕ አካላት ተናገሩ፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ለመጣው የኢንዱስትሪ ብክለት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው የተባሉ ስድስት የቆዳ ፋብሪካዎች እንዲታገዱ ውሳኔ ቢተላለፍም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጉዳዩን አመዛዝኖ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የተላለፈውን ውሳኔ ተፈጻሚ እንዳይሆን አገደ፡፡ 

በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቁጥጥር ላይ የሚሠራውና ‹‹ሲ-40 የአየር ንብረት ፎረም›› የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም፣ በአየር ንብረት ጥበቃ በተለይም ከብክለት ነፃ በሆነው የኤሌክትሪክ ባቡር ትራንስፖርቷ ሳቢያ እ.ኤ.አ. በ2016 ውድድር አዲስ አበባ ከተማ ማሸነፏ ተገለጸ፡፡ 

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ቁጥር 141352 አራጣ በማበደር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማት ጀመሩ፡፡ 

በመገናኛ አካባቢ የተገነባው በአንድ ጊዜ 90 ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ ባለ 15 ደረጃ ያለው ስማርት የመኪና ማቆሚያና 50 መኪናዎችን የመያዝ አቅም ያለው የመሬት ላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ሐሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም. የሙከራ ሥራውን መጀመሩ ተገለጸ፡፡ 

Pages