- የሦስት ሆቴሎች ስምምነት ተፈረመ 

በዓለም ስማቸው ከሚጠራ ትልልቅ ብራንድ ሆቴሎችን ከሚያስተዳድሩ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው አኮር ሆቴልስ ግሩፕ፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እንዲከፈቱ ከተስማማባቸው በተጨማሪ ሦስት አዳዲስ ብራንዶችን ለማምጣት ተስማማ፡፡

​የውጭ ዜግነት ባላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተይዘዋል የተባሉ  የባንክና ኢንሹራንስ አክሲዮኖች እንዲሸጡ በተሰጠው ውሳኔ መሠረት፣ አዋሽ ባንክ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው ጨረታ አንድ ሺሕ ብር ዋጋ ላለው አንድ አክሲዮን እስከ 14 ሺሕ ብር ድረስ የመጫረቻ ዋጋ ቀረበ፡፡

​በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነቡና ለተጠቃሚዎች ከተላለፉ ከኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚወጣ ፈሳሽ ቆሻሻ፣  በዘመናዊ መንገድ ተጣርቶ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ፡፡

​በኢትዮጵያ የታሪክና ማኅበራዊ ጥናት ሁነኛ ሥፍራ የነበራቸው ዕውቁ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ሥርዓተ  ቀብር፣ ሰኞ የካቲት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፈጸማል፡፡ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ያረፉት ባለፈው ሐሙስ የካቲት 9 ቀን ነበር፡፡

​የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ አዲስ አበባን ጨምሮ ለ22 ከተሞች የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚውል የ450  ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማግኘት ከዓለም ባንክ ጋር ድርድር እያካሄደ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

​የአዲስ አበባ ከተማን የፍሳሽ ቆሻሻ በመስመር የማንሳት አቅም አሁን ካለበት  አሥር በመቶ ሽፋን፣ ወደ 64 በመቶ ከፍ የሚያደርጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ከስድስት ቢሊዮን ብር በበለጠ ወጪ እየተካሄደ ነው፡፡

Pages