የኢትዮጵያና የኬንያ መንግሥታት ከኬንያ ላሙ ወደብ አዲስ አበባ የሚደርስ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ግንባታ ስምምነት እንደተፈረመ ተደርጎ የተሰራጨው ዘገባ ስህተት መሆኑን የማዕድን፣ ፔትሮሊየምና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከግል ባንኮች ቀዳሚ በመሆን ላለፉት 22 ዓመታት በባንክ ኢንዱስትሪው ሲንቀሳቀስ የቆየው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በተገባደደው በጀት ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ በማስመዝገብ ከግል ባንኮች ቀዳሚ የሚያደርገውን ሪከርድ መያዙ ታወቀ፡፡

በሽብር ድርጊት ወንጀት ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ እንዲከላከሉ ብይን በተሰጠባቸው በእነ ዘመኑ ካሴ መዝገብ አቶ አሸናፊ አካሉ፣ አቶ ደህናሁን ቤዛ፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁንና አቶ አንሙት የኔዋስ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት አዘዘ፡፡

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) አመራር የነበረው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ከአገር ወጥቶ ሕክምና ለማግኘት የተጣለበት ዕግድ እንዲነሳለት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያመለከተ ቢሆንም፣ የተሟላ ሰነድ እንዳልቀረበለትና ተሟልቶ ሲቀርብለት ጥያቄውን የሚያይ መሆኑን፣ ፍርድ ቤቱ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. አስታወቀ፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚኘው የጎንደር ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለኩላሊት ሕክምና የሚያስፈልጉ የዘመናዊ መሣሪያዎች ባለቤት መሆን ቢችልም፣ መሣሪያዎችን በሥራ ላይ ለማዋል የኃይል እጥረት እንዳጋጠመው አስታወቀ፡፡

Pages