​አዋጅ ወጥቶለትና መዋቅር ተዘጋጅቶለት በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ ሊደረግ የነበረው ማኅበራዊ የጤና መድን ሥራ ላይ  እንዳይውል እክሎች እንደገጠሙት፣ በዚህም ምክንያት በሌላ አሠራር ሊተካ እንደሚችል የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ለፓርላማው ይፋ አደረጉ፡፡

በደካማ የሥራ አፈጻጸም ሲወቅሱ የቆዩት  የሆርቲካልቸር ልማት ኤጀንሲና  የግብርና ኢንቨስትመንትና መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ተዋህደ፣ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሆነ መሥሪያ ቤት ተቋቋመ፡፡

​ከመሀል አዲስ አበባ በመልሶ ማልማት ፕሮግራም የተፈናቀሉ ነጋዴዎች ግንባታ የሚያካሂዱበት ምትክ ቦታ እስካሁን ድረስ ስላልተሰጣቸው  ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን፣ ለግንባታ ያዋጡት ገንዘብም ለዓመታት ያለሥራ መቀመጡን ገለጹ፡፡

​ከሦስት ዓመታት በፊት በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ሸዋበር መስጊድ አካባቢ ሰኔ 27  ቀን 2005 ዓ.ም. ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ አዛውንቱን ሼክ ኑሩ ይማምን በሁለት ጥይት ተኩሶ በመግደል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው 14 ተከሳሾች፣

Pages