የአገር ውስጥ ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ ለማርካትና በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ድርሻ ለመያዝ የተጀመረው የስኳር ልማት ዘርፍ፣ ከወዲሁ በተለያዩ ችግሮች በመተብተቡ መንግሥት 115 ሺሕ ሔክታር መሬት ተቀንሶ ለጥጥ ልማት እንዲውል ወሰነ፡፡ 

ሐሰተኛ ማስረጃዎችን በማቅረብና የቡና ላኪነት ፈቃድ በማውጣት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ውጭ የሚላክ ቡና ገዝተው መላክ ሲገባቸው በመደበቅ ሳይልኩ በመቅረታቸው፣ መንግሥት ማግኘት የነበረበትን ከ139 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል

​ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በመደረጉ ሳቢያ በአንዳንድ የምግብ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ ከዚህ በኋላም ዕርምጃ እንደሚወስድ ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

​እ.ኤ.አ. በ2016 በኢትዮጵያ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ይዞታ የዳሰሰው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርት በዓመቱ ለእስር የተዳረጉ ከ10,000 በላይ ዜጎች ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ፣ የሕግ ማማከር አገልግሎት እንዳላገኙና ክስ እንዳልተመሠረተባቸው ገለጸ፡፡

Pages