በአዲስ አበባ ሲካሄድ በቆየው 29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ፣ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴና ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በኅብረቱ ግቢ ውስጥ የመታሰቢያ ሐውልት እንዲቆምላቸው ተወሰነ፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት በቅርቡ በዕጣ ይተላለፋሉ እየተባለ ሳይተላለፉ የቆዩ በሰንጋ ተራና ክራውን ሳይቶች የተገነቡ 972 ቤቶችና ከ320 በላይ የንግድ ቤቶች፣ በመጪው ቅዳሜ ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. በዕጣ እንዲተላለፉ ተወሰነ፡፡

በምሕረት ሞገስና በውድነህ ዘነበ

የፌዴራል መንግሥት ላለፉት በርካታ ዓመታት በሥሩ የቆዩትን ግዮን ሆቴሎች ድርጅትና የፍልውኃ አገልግሎት ድርጅት፣ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነ፡፡

  • ኤርትራ የአፍሪካ ኅብረትን እውነታ አፈላላጊ ቡድን አልቀበልም አለች

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ከያዙ ሁለት ጊዜ እስራኤልን በመጎብኘታቸው፣ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት በተለየ ሁኔታ እንደሚያዩት የፍልስጤም ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡

ከአዋሽ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ወልዲያ ቅርንጫፍ ያለምንም ማመልከቻና ማስያዣ፣ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ በመበደርና ባንኩ ማግኘት የነበረበትን ኮሚሽን በማሳጣት የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  • ግንባታው ከፈቀደለት የህንዱ ኩባንያ ይነጠቃል

የህንድና የአሜሪካ ኩባንያዎች በሽርክና ያቋቋሙት ኬይ ግሩፕ ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በጻፈው ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያንና የህንድን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት ለማስጠበቅ ለበርካታ ዓመታት ሲጓተት ለቆየው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ መፍትሔ ይዞ መቅረቡን ገለጸ፡፡

Pages