መንግሥትን በኃይል የመለወጥ የፖለቲካ ዓላማ በመያዝ ታኅሳስ 25 ቀን 2009 ዓ.ም. በአማራ ክልል በሚገኙ የባህር ዳርና የደብረ ታቦር ከተሞችን ጨምሮ፣ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች አመፆችና ረብሻዎች እንዲፈጠሩ የማደራጀትና የማንቀሳቀስ ተግባር ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ 17 ሰዎች በሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በአራጣ አበዳሪነት በፍርድ ቤት ክስ ተመሥርቶባቸው ጥፋተኛ በመባል የ25 ዓመታት እስራትና የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ንብረታቸው እንዲወረስ የተፈረደባቸው አቶ ከበደ ተሠራ (ወርልድ ባንክ) ንብረት የነበረውንና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሲወዛገብበት የነበረው ሕንፃ በ72.7 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ለጨረታ ቀርቦ፣ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በ680 ሚሊዮን ብር የጨረታው አሸናፊ ሆነ፡፡

Pages