የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያ ሊመጡ መሆኑ ታወቀ፡፡ ኮሚሽነሩ የሚመጡት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ለመነጋገር ነው ተብሏል፡፡ 

ዓመታዊ የሽያጭ ገቢያቸው 100,000 ብር የነበረው በአዲሱ የግብር አዋጅ ወደ 500,000 ብር ከፍ ካለ በኋላ፣ ዝቅተኛ ግብር ከፋዮችና የሚመለከታቸው ነጋዴዎች አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ተግተው መሥራት እንዳለባቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡ 

የአገሪቱን የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች ማለትም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ 38(1)፣ 27(1)፣ 238(1ሀ እና ለ)ን በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት ፈጽመዋል በመባል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የቀረበባቸው ክስ እውነትነት የሌለውና ተጣሞ የቀረበ መሆኑን ለፍርድ ቤት ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግል የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚሆኑ የብድር ጥያቄዎችን እንደማያስተናግድ ያስተላለፈው ውሳኔ ድንጋጤ ፈጠረ፡፡ የፕሮጀክት ብድር ጥያቄዎችም ወደ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንዲዛወሩ ተወስኗል፡፡

Pages