በአዲስ አበባ ከተማ መገናኛ ድልድይ አካባቢ፣ በአራት ዓመት ውስጥ የታየ ለውጥ፡፡ በደቡብ አቅጣጫ ወደ ኢምፔሪያል- ቦሌ መንገድ ግራና ቀኝ የቀድሞና  ያሁን ገጽታን ልብ ይሏል፡፡

​በአፍሪካ ኅብረት 28ኛው የመሪዎች ጉባኤ ላይ ከተገኙት  መካከል (በግራ) የደቡብ ሱዳንና የሱዳን ፕሬዚዳንቶች ሳልቫ ኪር እና ኦማር ሀሰን አልበሽር፤ የዚምባቡዌና የግብፅ ፕሬዚዳንቶች ሮበርት ሙጋቤ እና አብዱልፈታህ አልሲሲ እጅ ሲነሣሱ፡፡ 

ፎቶ በናሆም ተስፋዬ  

​የገና በዓል መገለጫ ከሆኑት አንዱ  ዛፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ጥድ እየተቆረጠ በልዩ ልዩ ማሸብረቂያዎች ይዋብ ነበር፡፡ አሁን አሁን አርቲፊሻል ዛፎች በየቦታው ነግሰው ይታያሉ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና የንግድ ስፍራዎች ከውጭ በሚገቡት ሰው ሠራሽ የገና ዛፎች ሲጨናነቁ፣ ወጣቱ ደግሞ ቦሌ  መድኃኔዓለም አካባቢ ጥግ ይዞ ሁለት ሊትር ስፕራይት ከሚይዘው የፕላስቲክ ዕቃ የገና ዛፍ እየሠራ ይታያል፡፡ ለቋሚውም ሸምበቆ ይጠቀማል፡፡ የአንዱ ዋጋም 60 ብር ነው፡፡ ፎቶ በዳንኤል ጌታቸው

Pages