​የገና በዓል መገለጫ ከሆኑት አንዱ  ዛፍ ነው፡፡ ቀደም ሲል ጥድ እየተቆረጠ በልዩ ልዩ ማሸብረቂያዎች ይዋብ ነበር፡፡ አሁን አሁን አርቲፊሻል ዛፎች በየቦታው ነግሰው ይታያሉ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ዋና የንግድ ስፍራዎች ከውጭ በሚገቡት ሰው ሠራሽ የገና ዛፎች ሲጨናነቁ፣ ወጣቱ ደግሞ ቦሌ  መድኃኔዓለም አካባቢ ጥግ ይዞ ሁለት ሊትር ስፕራይት ከሚይዘው የፕላስቲክ ዕቃ የገና ዛፍ እየሠራ ይታያል፡፡ ለቋሚውም ሸምበቆ ይጠቀማል፡፡ የአንዱ ዋጋም 60 ብር ነው፡፡ ፎቶ በዳንኤል ጌታቸው

​ሐረር ባስተናገደችው 11ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል፣ ከተገኙት ታዳሚዎች ውስጥ ከደቡብ ኦሞ ዞን  የመጣችው ወ/ሮ ዙፋን (በቀኝ) ትገኝበታለች፡፡

ሁሉም ሥራ ራሱን የቻለ ባለሙያ ይሻል (ይፈልጋል) እንጨት  መፍለጥ እንኳ! እንጨት ያለ ሙያተኛው ቢፈለጥ በመጥረቢያው እግር ይጎዳል ወይም እንጨቱ ዘሎ (ተፈናጥሮ) ዓይን ወይ ጥርስ ወይ ግንባር ሊመታ ይችላል፡፡ 

ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ የተከናወነው ታላቁ ሩጫ  በኢትዮጵያ ተሳታፊዎች ከያዟቸው ማድመቂያዎች አንዱ፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ቱሪዝም መለያ (ብራንድ) ‹‹ኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጂንስ›› ነበር፡፡

Pages