ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያን ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኙት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ፣ በመጀመሪያ ቀን ውሏቸው ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ጋር ተገናኝተዋል፡፡ ባጋጣሚው በቀድሞው ኢዮቤልዩ ቤተመንግሥት የሚገኙትን አንበሶችንም ቃኝተዋል፡፡

በብዙ ሰዎች ስብስብ የአውሮፕላን ቅርፅ በመሥራት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጊነስ ወርልድ ሪኮርድን ይዟል:: ኤርባስ ኤ 350 ኤክስ ደብሊው ቢ (A 350xWB)
በማስመሰል በሰዎች የተሠራው ቅርፅ በአየር መንገዱ ጊቢ ውስጥ ለእይታ የቀረበ ሲሆን፣ ሰኔ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ተመዝግቧል::

ከኢምፔሪያል ወደ 17 ጤና ጣቢያ በሚወስደው መንገድ ለብስክሌት መጋለቢያ የተዘጋጀው መንገድ፡፡

ይህች ከተማ በህዳሴ ግድብ ውኃ ተጠራቅሞ የሚጨርስባት ከተማ ስትሆን የአሁኗን ሐዋሳ እንደምትመስል ይጠበቃል

ፎቶ በታምራት ጌታቸው

Pages