ሰላም! ሰላም! ‹‹ሐበሻ ‘ጥበቡን’ ጥበብ ቀሚስ ላይና ምሳሌ ላይ ጨረሰው›› ስል ባሻዬ ሰምተውኝ ኖሮ፣ ‹‹ወሬስ የት ሄዶ?›› ብለው ቀብ አደረጉኝ።  

ሰላም! ሰላም! ‹‹የዚህ ዓለም ደስታ ደካማ ነው›› ማን ነበር ያለው? አዎ፣ የመጨረሻው  ንጉሠ ነገሥታችን ናቸው። ይኼውላችሁ ያ አብዮት ፍሬውንም ገለባውንም ጥሩ አድርጎ ከትውስታችን ገርስሶታል ማለት ነው።

ሰላም! ሰላም! ሁዳዴ እንደ ምንም ድሆ ገባ።  እኛም ሁለት ወር ኑሮን በፈቃደኝነት  ጭር ልናደርገው ተሰናዳን። አቤት ሆድና ሰው ተባለ። ከውስጥ የሚወጣ እንጂ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰውን አያረክሰውም እንዳላለን ቃሉ ብሎ ብሎ ትዝብትም ወደ ሆድ ገባ። 

​ሰላም!  ሰላም! ሰው ‹በፍቅር ቀን› አብዶ አሳበደን እኮ። ያብዛልን ነው። ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀን የሩኒና የሮናልዶን ጫማ ቁጥር  በምንሰበክበት አገር ለፍቅር አንድ ቀን መመደቡ በራሱ ያበሳጫቸው አጋጥመውኛል።

​ሰላም! ሰላም! “ኧረ እኔስ ፈራሁ. . .” አለች አሉ ሚስቲቱ። ባል ተሰማዋ።  በትንሽ ትልቁ እየተሰማን አንዳንዴ እኮ ባሎች ስንባል እናበዛዋለን። እና “እንዴት! እንዴት! ምን ለማለት ነው እኔ እዚህ ተቀምጨ ፈራሁ ማለት?” ይላል። 

​ሰላም! ሰላም! ምን ሰላም አለ ዋጋ እያሻቀበ? አትሉኝም። ባለፈው እህል ቅጠል የማይል ፍርፍር ማንጠግቦሽ ሠርታ ብታቀርብልኝ ማላመጥ እንኳ እስኪያቅተኝ አፌ ውስጥ ሳንገዋልለው ነበር። 

​ሰላም! ሰላም!  መቼስ አንዳንዴ ዓለም ምን ፀሐይ  ብትመስል ሰው ሐሳብና ብጤ ሲያጣ ቀን ይጨልምበታል። ይሰውራችሁ ነው። እና አንድ ሰውዬ ነው አሉ። ቀን ጨለመበት። 

​ሰላም! ሰላም! በገና ማግሥት ማንጠግቦሽ ያለልማዷ ሬት ሬት  የሚል ቡና አፍልታ ትግተናለች። ባሻዬ ከእነ ልጃቸው ደግሞም እኔ ተሰባስበናል።

Pages