ሰላም! ሰላም! ሁዳዴ እንደ ምንም ድሆ ገባ።  እኛም ሁለት ወር ኑሮን በፈቃደኝነት  ጭር ልናደርገው ተሰናዳን። አቤት ሆድና ሰው ተባለ። ከውስጥ የሚወጣ እንጂ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰውን አያረክሰውም እንዳላለን ቃሉ ብሎ ብሎ ትዝብትም ወደ ሆድ ገባ። 

​ሰላም!  ሰላም! ሰው ‹በፍቅር ቀን› አብዶ አሳበደን እኮ። ያብዛልን ነው። ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀን የሩኒና የሮናልዶን ጫማ ቁጥር  በምንሰበክበት አገር ለፍቅር አንድ ቀን መመደቡ በራሱ ያበሳጫቸው አጋጥመውኛል።

​ሰላም! ሰላም! “ኧረ እኔስ ፈራሁ. . .” አለች አሉ ሚስቲቱ። ባል ተሰማዋ።  በትንሽ ትልቁ እየተሰማን አንዳንዴ እኮ ባሎች ስንባል እናበዛዋለን። እና “እንዴት! እንዴት! ምን ለማለት ነው እኔ እዚህ ተቀምጨ ፈራሁ ማለት?” ይላል። 

​ሰላም! ሰላም! ምን ሰላም አለ ዋጋ እያሻቀበ? አትሉኝም። ባለፈው እህል ቅጠል የማይል ፍርፍር ማንጠግቦሽ ሠርታ ብታቀርብልኝ ማላመጥ እንኳ እስኪያቅተኝ አፌ ውስጥ ሳንገዋልለው ነበር። 

​ሰላም! ሰላም!  መቼስ አንዳንዴ ዓለም ምን ፀሐይ  ብትመስል ሰው ሐሳብና ብጤ ሲያጣ ቀን ይጨልምበታል። ይሰውራችሁ ነው። እና አንድ ሰውዬ ነው አሉ። ቀን ጨለመበት። 

​ሰላም! ሰላም! በገና ማግሥት ማንጠግቦሽ ያለልማዷ ሬት ሬት  የሚል ቡና አፍልታ ትግተናለች። ባሻዬ ከእነ ልጃቸው ደግሞም እኔ ተሰባስበናል።

​ሰላም! ሰላም! ይኼው እንደምታዩት ከተማው ሰፍቷል። ማማር አለማማሩን ለባለሙያ  እንተወው ብዬ እኮ ነው። ለእኛ በሚመቸንና በምናውቅበት ብሂል ለጨዋታ ስናመቻቸው፣ የከተማውን መስፋት ተከትሎ ነዋሪው በሁለት ተከፈሏል አሉ። 

​ሰላም! ሰላም! ተስፋን በውስጣችን የመለኮስ ባለሙሉ ሥልጣን ባለቤት ነንና እነሆ ዛሬን በደስ ደስ እንጀምረው። ምን አባቱ።  ስንት ዓመት ይኖራል? ስላችሁ ʻተኑሮ ተሞቷልʼ እንዳትሉኝና እንዳይብሰኝ አደራ።

​ሰላም! ሰላም! በቅርቡ እነ አምታታው በከተማ መኪና እንጭንልሃለን ብለው  ሙልጭ አድርገው የበሉት ወዳጄ ከፀበል መመለሱን ሰማሁና ልጠይቀው ሄድኩ። 

Pages