‹‹እንደነ ቻይና ያሉ አገሮች እንደኛ በነበሩበት ወቅት የሴቶቻቸውን ፀጉር ሸጠው ነው ችግራቸውን የፈቱት፡፡››

​‹‹ሰዎች ዶሮዎቼን ሊሰርቁ ይችላሉ፤ ሰዎች በጎቼን ሊሰርቁ ይችላሉ፤ ዕድሜዬን ግን ሊሰርቁ አይችሉም፡፡››

​‹‹ግልገል ጊቤ ፫ (3) የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የኃይል እጥረት በመቅረፍ ረገድ የቁርጥ ቀን ደራሽነቱን አረጋግጧል፡፡››

‹‹ፕሬዚዳንት ፊደል ካስትሮ ኢትዮጵያዊያን የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለመከላከል ባደረጉት ተጋድሎ ያለማወላወል ከጎናቸው የተሠለፉ ታላቅ ወዳጅ ሲሆኑ፣ ይህንንም ታሪክ ምንጊዜም ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡››

​‹‹በሰብአዊ መብቶችና በሰዎች ክብር ላይ የተመሠረቱትን፣ ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸውን የግብረገብ (ሞራል) እሴቶች ይጠብቁ ዘንድ ኃላፊነት አለብዎት፡፡››

​‹‹ሰዎች ለተሻለ ሕይወት ከአንድ አገር ወደ ሌላው ሲሰደዱ፣ ስለራሳችን ጥቅም ብቻ ሳይሆን በማሕጸን ውስጥ ስላለ ሕፃንም ይሁን ስለ እናቱ አልያም ስለ ቤተሰቡም ማሰብ አለብን፡፡ 

​‹‹አሁን የትኛው ሰው ነው፣ በቆየ ፍቅሩ ላይ ተመሥርቶ ካልሆነ በስተቀር፣ ሚዲያ ውስጥ መግባት አዋጪ ነው ብሎ፣ ኢንቬስት አድርጐና ዕዳ ውስጥ ገብቶም ቢሆን ይህን ሥራ ለመሥራት የሚንቀሳቀሰው?››

Pages