​ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ያወጡት መግለጫ ተነቧል፡፡ ድርድሩ የተሳካ ይሆን ዘንድ የሁሉም አካላት ድርሻ እንዲያይል የሚጠይቅ ነው፡፡ ኢሕአዴግም እንደ ከዚሁ በፊት ለይስሙላ፣ ለሚዲያ ፍጆታና ለማይረባ የፖለቲካ ትርፍ እንዳያውለው ያሳስባል፡፡

​‹‹በሃያ ሰባት ዓመታት የስደት ሕይወቴ  የተማርኩት አገር አልባና ባይተዋር ሆኖ መኖር የቁም ሞት መሆኑን ነው፤›› የሚሉት አብዱላሂ ሐሰን ጌዶ አዲስ አበባ ቦሌ በተለምዶ 24 ቀበሌ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ውስጥ የሚኖሩ የ67 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሶማሊያ ስደተኛ ናቸው፡፡

ግብፅ ከዓባይ ወንዝ የምታገኘው ዓመታዊ የውኃ ድርሻ አንድ ጠብታ እንኳን ቢቀንስ ወታደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ ከአገሪቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመምከር የሚታወሱት የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሐመድ ሙርሲ፣ ዳግም በተቀሰቀሰው የግብፃውያን ማዕበል ከመጠለፋቸው ጥቂት አስቀድሞ የመከላከያ ሠራዊቱ አገሪቱን ለማዳን በወሰደው ዕርምጃ ቤተ መንግሥታቸውንና ሥልጣናቸውን ለቀዋል፡፡

​ተቀማጭነቱ በአዲስ አበባ የሆነው 55 አባል አገሮች የሚሳተፉበት የአፍሪካ  ኅብረት በፖለቲካዊና በአስተዳደራዊ አካላት የተዋቀረ ተቋም ቢሆንም፣ በበርካታ አፍሪካውያን ዘንድ እዚህ ግባ የሚባል ተቀባይነት የለውም፡፡ 

​ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን ያልረገጡት የተቃዋሚ ቡድኑና የኑዌሮች መሪ ዶ/ር ሪክ ማቻር ጁባ እንደሚገቡ ሲገለጽ፣ ለደቡብ ሱዳን ችግር መፍትሔ ለመሻት ተስፋ ፈንጥቆ ነበር፡፡  

​ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ‹ደይሊ ኒውስ› የተባለ አንድ የግብፅ ጋዜጣ አንድ ዜና ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ደቡብ ሱዳን ጠንካራ ብሔራዊ የጦር ኃይል ለመገንባት የግብፅ ወታደራዊ ዕርዳታ ትሻለች፤›› የሚል፡፡ 

Pages