​ለሁለት ዓመት ተኩል ያህል የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባን ያልረገጡት የተቃዋሚ ቡድኑና የኑዌሮች መሪ ዶ/ር ሪክ ማቻር ጁባ እንደሚገቡ ሲገለጽ፣ ለደቡብ ሱዳን ችግር መፍትሔ ለመሻት ተስፋ ፈንጥቆ ነበር፡፡  

​ባለፈው ዓመት ጥር ወር ላይ ‹ደይሊ ኒውስ› የተባለ አንድ የግብፅ ጋዜጣ አንድ ዜና ይዞ ወጥቶ ነበር፡፡ ‹‹ደቡብ ሱዳን ጠንካራ ብሔራዊ የጦር ኃይል ለመገንባት የግብፅ ወታደራዊ ዕርዳታ ትሻለች፤›› የሚል፡፡ 

​የፖለቲካ ተንታኞች በኢሕአዴግ የምትመራው ኢትዮጵያ ካለፉት ሥርዓቶች በወረሰችው ፈላጭ  ቆራጭና  አምባገነናዊ ባህል፣ ሕገ መንግሥቷና ዝርዝር ሕጐቿ በሚሰብኩት ጠንካራና ጤናማ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ መካከል የምትዋልል እንደሆነች ያስረዳሉ፡፡

የደጋው ክፍል ኤርትራውያን አብዛኞቹ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው፡፡ የጊዜ አቆጣጠራቸውም እንደ ኢትዮጵያ ነው፡፡ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያከብራቸው ሃይማኖታዊ በዓላት በኤርትራ ደገኛ ትግረኛ ተናጋሪ የኅብረተሰብ ክፍልም ይከበራሉ፡፡

ሰኞ ጥር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከረጅም ጊዜ በኋላ በተሰጠው በዚህ መግለጫ ጋዜጠኞች አንገብጋቢና በቅድሚያ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ያሉዋቸውን ጥያቄዎች አቅርበዋል፡፡ 

​‹‹እ.ኤ.አ. በ2040 በውኃ እጦት የሚሰቃዩ አሥር ተቀዳሚ አገሮች  የትኞቹ ናቸው?››

ጋዜጠኛና ጸሐፊው ዳንኤል ካሊናኪ ይህን ጥያቄ ያቀረበው ናይል ቤዚን ኢንሺየቲቭ (ኤንቢአይ) እ.ኤ.አ. ከታኅሳስ 12 እስከ 16 ቀን 2016 በሩዋንዳ ኪጋሊ አዘጋጅቶት ለነበረው ክልላዊ የሚዲያ ሥልጠና ተሳታፊዎች ነው፡፡ 

​የዛሬ 25 ዓመት ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ የመቃወም መብት በመርህ ደረጃ የተከለከለ አይደለም፡፡ በተግባር ግን መቃወም ያለ ብዙ ዋጋ የሚፈጸም እንዳልሆነ በርካታ አብነቶች ይቀርባሉ፡፡

Pages