የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዙሪያው ለሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተሞች ንፁህ የመጠጥ ውኃ ማቅረብ የሚያስችል አዲስ ዕቅድ አፀደቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ይህንን ዕቅድ ለማሳካት አስተዳደሩ 660 ሚሊዮን ብር በጀት ይዞ ወደ ግንባታ እየገባ ነው፡፡

ኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በደረቅ ወደቦች ያላግባብ የሚከማቹ ኮንቴይነሮች እንዳይኖሩ ለማድረግ፣ የደረቅ ወደቦችን የኪራይ ዋጋ ለመጨመር ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ጋር እየመከረ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ ቁጥር 141352 ውስጥ ተካተው አራጣ በማበደር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤት አቶ ከተማ ከበደ፣ የመጨረሻ የመከላከያ ምስክራቸውን አሰሙ፡፡

መንግሥት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች አሠራር ጋር በተያያዘ አዳዲስ ፖሊሲዎችን፣ አገልግሎት ሰጪ መንግሥታዊ ተቋማትም በአዲስ ይዘት ወደ ሥራ የሚገቡበትን አሠራር፣ ለአገር ውስጥ አምራቾችም ልዩ ማበረታቻዎችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና 16 ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ድርድርና ውይይት ለማድረግ በተስማሙት መሠረት፣ የሕገ መንግሥቱ የተለያዩ አንቀጾችን ከማሻሻል አንስቶ እስከ የባህር በር ጥያቄ የተካተተበት 13 ነጥቦችን የያዘ ረቂቅ አጀንዳ ለውይይት  ቀረበ፡፡

Pages