የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ተወካይ ማርጋሬት ኦዱክ (ዶ/ር)፣ የዓለም አካባቢ ቀን በአዲስ አበባ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም. ሲከበር ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ተወካይዋ አክለውም፣ የሰው ልጅ ጤናው ተጠብቆ በሰላምና በደኅንነት እንዲኖር ከፈለገ ምድርን ከብክለት የፀዳች ማድረግ ይጠበቅበታል ብለው፣ ኅብረተሰብ እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ የሰው ልጆች ድርጊት የተነሳ የተበከለች ምድር ሳይሆን የፀዳች ምድር ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የአረጓዴ ልማትን በመተግበርና አመራር በመስጠት የምታከናውነው ሥራ የሚበረታታ ነውም ብለዋል።