Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከባድ ዝናብ እየጣለ ከመኪናቸው በመውረድ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው በወቅታዊ ዝናብ ዙሪያ ከባለቤታቸው ጋር እየተጨዋወቱ ነው]

  • የዘንድሮ ክረምት ከበድ ብሎ የመጣ ይመስላል አይደል?
  • እንዴት አወቅህ? 
  • ይኸው ገና ሰኔ ሳይገባ ጎርፍ እያስቸገረን አይደለም እንዴ? 
  • ቦዮቹ በቆሻሻ ስለተደፈኑ ይሆናላ?
  • እንጂ ክረምቱ ከባድ ስለሆነ አይደለም እያልሽ ነው? 
  • እሱንማ እንዴት አውቃለሁ?
  • በከባዱ እየዘነበ እያየሽ አይደለም እንዴ? 
  • ከባድ ዝናብ እየጣለ መሆኑንማ እያየሁ ነው።
  • ታዲያ ምንድነው የምትይው?
  • መለየት አልቻልኩም ማለቴ ነው።
  • ዝናብ መሆኑን መለየት አልቻልሽም?
  • እሱማ እንዴት ይጠፋኛል?
  • እና ምኑን ነው መለየት ያልቻልሽው?
  • የማን እንደሆነ። 
  • ምኑ? 
  • ዝናቡን ነዋ፡፡
  • እንዴት?
  • ምን እንዴት አለው፣ ባለፈው የእኛ ዝናብ ነው ስትሉን አልነበረም እንዴ?
  • እህ… የዝናቡን ባለቤት ነው መለየት የተቸገርሽው?
  • ታዲያ… የብልፅግና ዝናብ ይሁን የክረምት ዝናብ መለየት ተቸገረን እኮ? 
  • አይ አንቺ… እና እንዴት ነው የዝናቡን ባለቤት የምትለይው? 
  • እኔ እንኳን ባልችልም በቀላሉ ይለያል ሲባል ሰምቻለሁ።
  • እንዴት ነው በቀላሉ የሚለየው?
  • በኪሎ በቀላሉ ይለያል አሉ።
  • በኪሎ? 
  • አዎ። እንደዚያ ሲባል ሰምቻለሁ። 
  • ዝናብ በኪሎ?
  • አዎ። ለምሳሌ የእናንተ አራት ኪሎ ነው የሚባለው አሉ። 
  • አራት ኪሎ? ለምን?
  • እዚያ ስለማይጥል። 

  [ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊው ዝናብ ዙሪያ ከባለቤታቸው እየተጨዋወቱ ቴሌቪዥኑን ሲከፍቱ ቃል አቀባይዋ የሰጡት መግለጫ እየተላለፈ ዓይተው ከባለቤታቸው ጋር መከታተል ጀመሩ]

  • ሰማህ… ሰማህ?
  • ምንድን? ቃል አቀባይዋ ያሉት ነው? 
  • አዎ። አሁን ነው ክረምቱ ከባድ ማለት!
  • ምንድነው ያሉት?
  • ክረምቱን ተገን አድርገው ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት ላይ ናቸው እያሉ ነው።
  • አያደርጉትም? 
  • ለምን? 
  • አይሆንም ስልሽ? 
  • እኮ ለምን?
  • የቀጣዩ ዓመት በጀት ለፓርላማ ሲቀርብ የተገለጸው ያንን የሚያመለክት አይደለም። 
  • በጀቱ ሲቀርብ ምንድነው የተባለው?
  • ጦርነት ቆሞ ሰላም እንደሚሰፍንና በቀጣዩ ዓመትም በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት ትኩረት እንደሚሰጥ ነው ታሳቢ የተደረገው። 
  • እንደዚያ ከሆነስ ጥሩ ነው ግን ….
  • ግን ምን?
  • ለምንድነው ከአንድ መንግሥት ሁለት የሚጣረሱ መረጃዎች የሚወጡት?
  • ምን ተጣረሰ?
  • አንዱ በክረምቱ ጥቃት ለመክፈት ዝግጅት እያደረጉ ነው ይላል።
  • እሺ…
  • ሌላው ደግሞ በቀጣዩ ዘመን ሰላም ሰፍኖ ለመልሶ ግንባታ ትኩረት የሰጠ በጀት አጽድቁልኝ ይላል። ግራ እኮ አጋባችሁን?
  • አይዞሽ አትስጊ ሰላም ይሆናል። 
  • የቀረበው በጀት ግን ያንን የሚያመላክት ነው?
  • አዎ። ትልቅ በጀት ነው እንዲጸድቅ የተጠየቀው።
  • ትልቅ በጀት መጠየቁ ሰላም እንደሚሆን ያሳያል ብለህ ነው?
  • እንደ እኔ እንደ እኔ ትልቅ በጀት መጠየቁ ፊታችንን ወደ ልማት ማዞራችንን ይጠቁማል ባይ ነኝ።
  • ስንት ተጠየቀ?
  • 6 ቢሊዮን ብር።
  • አጠቃላዩ ማለት ነው?
  • አዎ። አጠቃላይ ነው።
  • ከዚህ ውስጥ ለመከላከያ ስንት ተያዘ? 
  • መቶ ቢሊዮን። 
  • ምን…?
  • ምነው ደነገጥሽ?
  • በጀቱ ወደ ልማት መዞራችንን ይጠቁማል ስትል አልነበረም እንዴ?
  • አዎ። ብያለሁ፡፡
  • ይኼ ልማትን ይጠቁማል?
  • እኔ ግን አላልኩማ፡፡
  • ምንድነው ያልከው ታዲያ?
  • ልማት ሳይሆን ወደ ልማት መዞራቸንን ይጠቁማል ነው ያልኩት።

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...

  አዲስ አበባ እንዳይገቡ በተከለከሉ ዜጎች ጉዳይ የኦሮሚያና አማራ ክልሎች ተወያይተው ችግሩ እንዲፈታ አደረጉ

  ለሳምንታት በርካታ ቅሬታ ሲነሳበት የነበረውና ከአማራ ክልል በደብረ ብርሃን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...

  ለኬንያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገበት

  በቅርቡ ሙሉ ለሙሉ ስምምነቱ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያና የኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...