Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበደራሽ ጎርፍ የተወሰደው ሕፃን አካል እስካሁን አልተገኘም

  በደራሽ ጎርፍ የተወሰደው ሕፃን አካል እስካሁን አልተገኘም

  ቀን:

  ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ሲወጣ ከታላቅ ወንድሙ ነጥሎ ደራሽ ጎርፍ የወሰደው ሕፃን አካል እስካሁን አልተገኘም፡፡

  ሕፃኑ ማርኮን ይድነቃቸው የአራት ዓመት ሕፃን ሲሆን፣ ከወላጆቹ ጋር በቤት የሚያሳልፉበትን ዕድሜ ጨርሶ አራት ዓመት ስለሞላው ታላቅ ወንድሙ በሚማርበት፣ በጉለሌ ክፍል ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ላዛሪስት (ካቶሊክ) ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም. መግባቱንና የኬጂ ተማሪ መሆኑን፣ የትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  ምክትል ርዕሰ መምህሩ ስለተፈጠረው ሁኔታ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ማለትም ሰኔ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ማርኮንና ታላቅ ወንድሙ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ውለው ከቀኑ 9፡45 ሰዓት ላይ ወደ ቤታቸው ለመሄድ ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወጥተዋል፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የሆነ ዝናብ ዘንቦ ስለነበር ከትምህርት ቤቱ መውጫ አጠገብ ያለው አስፋልት መንገድ በውኃ ተሞልቷል፡፡ ወንድማማቾቹ የመንገዱን ጠርዝ ይዘው ሲሄዱ ታላቅየው አዳልጦት ሲወድቅ፣ አጠገቡ የነበረው ሕፃን ማርኮን ሚዛኑን ይስትና የከተማው መንገዶች ባለሥልጣን ቆፍሮ ሳይዘጋው ክፍቱን ትቶት በነበረው የውኃ መውረጃ ቦይ (ጉድጓድ) ውስጥ ይወድቃል፡፡ በዚህ ጊዜ ከላይ ሞልቶ የሚፈሰው ውኃ ብዙም አቅም የሌለውን ሕፃን ማርኮንን ይዞት የውኃ ማውረጃ ቱቦ ውስጥ እንደከተተው ሲቃ እየተናነቃቸው ምክትል ርዕሰ መምህሩ አስረድተዋል፡፡

  በዕለቱ በአካባቢው ያሉ ወጣቶች ቱቦው ውስጥ ገብተው የተከተሉት ቢሆንም ሊያተርፉትና ሊያድኑት እንዳልቻሉ ገልጸው፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አባላት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ሠራተኞች ጭምር ሕፃኑን ለማትረፍና ቆይቶም አካሉን ለማግኘት ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱን ገልጸዋል፡፡

  ሮጦ ያልጠገበና ለወላጆቹም ሆነ በቅርብ ለሚያውቁት የትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ሰቀቀን መሆኑን፣ ወላጅ ለሆነ ሁሉ ትልቅ ድንጋጤ የፈጠረ አሳዛኝ ክስተት መሆኑንም አክለዋል፡፡

  ፍለጋው መቀጠሉንና እስከ አባ ሳሙኤል ድረስ ላለፉት አሥር ቀናት (እስከ ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ) መቀጠሉን፣ ነገር ግን ከትምህርት ቤቱ በተወሰነ ርቀት ላይ የሚገኝ ብዙ ቆሻሻ አጠራቅሞ የያዘ ጉድጓድ የሆነና ውኃ ያቆረ ቦታ ስላለ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ትብብር አድርጎ እንዲቆፈር ቢያደርግ፣ ምናልባት የሆነ ቦታ ላይ ተወትፎ ሊገኝ ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ወንዙ ቢቆፈር ያቆረው ውኃ ሊፈስ ስለሚችል በዚያውም በአካባቢው ላይ የሚፈጥረው ሽታ ሊጠፋ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

  ወላጆች የልጃቸውን አካል አግኝተውና በክብር አሳርፈው እንዲረጋጉ ማድረግ ካልተቻለ፣ እንኳን ለእነሱ ቀርቶ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ጥያቄና ስለሕፃኑ የሚነጋገሩት ጉዳይ ሁሉንም እረፍት የነሳና እጅግ አሰቃቂ መሆኑን አስረድተዋል፡፡  

  በትምህርት ቤቱ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች፣ እናቶችና አባቶች ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ተሰባስበው የሻማ መብራትና የፀሎት ፕሮግራም ማካሄዳቸውንና ፍለጋውም ሆነ ሐዘኑ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...