Monday, August 8, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም ሻምፒዎና መንገሣቸውን እያነሱ ደስታቸውን ሲገልጹ አገኟቸው]

  • እሰይ አገሬ… እሰይ አገሬ እልልል
  • ምን ተገኘ ደግሞ ዛሬ?
  • የአትሌቶቻችንን ድል ነዋ! በክፉ ሲነሳ የቆየውን የአገራቸውን ስም በወርቅ እያደሱ እኮ ነው? 
  • አየሽ፣ መንግሥት የአገራችን ችግር ያልፋል ስሟም በዓለም መድረክ ይናኛል የሚለው ዝም ብሎ አይደለም። 
  • እስኪ ደስታዬን አታዘባርቀው፡፡ 
  • ለአንቺ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡም እንዲህ እንደ አንቺ እንደሚደሰት ስለምናውቅ ነው… ያልፋል የምንለው።
  • ሌላ ምን እንዳስደሰተኝ ታውቃለህ?
  • ምንድነው? 
  • የአትሌቶቹ መተሳሰብ፣ አጠቃላይ የቡድኑ ፍቅር፣ አቤት ውበት… አቤት ውበት..!
  • አየሽ፣ መንግሥትም ለዚህ እኮ ነው ደጋግሞ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገረው? 
  • ስለየቱ ጉዳይ?
  • ስለመደመር።
  • ለምን አትተወኝም? 
  • ከተደመርን የማንወጣው ፈተና የለም አላልንም? ውጤቱ ይኸው!
  • እኔ ምለው?
  • ዛሬ ከቤት ጀምሩ ተብላችሁ ነው እንዴ?

  [ክቡር ሚኒስትሩ በአገሪቱ የተከሰተው ሁሉን አቀፍ የዋጋ ንረት እያደረሰ ያለውን ጫና ለማቅለል የተቋቋመው ኮሚቴን ሰብስበው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራትን እየገመገሙ ነው]

  • በደብዳቤ እንደተገለጸላችሁ የዛሬው ስብሰባ የተጠራው ይህ ኮሚቴ ከተቋቋመ በኋላ የዋጋ ንረት ጫናን ለማቅለል ያከናወናቸውን ተግባራት ለመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው። 
  • አዎ። ትክክል ነው ክቡር ሚኒስትር። 
  • መልካም። ተጨማሪ መታየት አለበት የምትሉት አጀንዳ ከሌላ በቀጥታ ወደ ተያዘው አጀንዳ መግባት እንችላለን።
  • መግባት እንችላለን ክቡር ሚኒስትር።
  • ጥሩ። ስለዚህ ኮሚቴው ያከናወናቸውን ተግባራትና የተገኙ ውጤቶችን እንዲያብራሩ የኮሚቴውን ሰብሳቢ እጋብዛለሁ።
  • ክቡር ሚኒስትር ወደ ማብራሪያው ከመግባቴ በፊት ማብራሪያ እንዲሰጥ የተፈለገው በምን ጉዳይ ላይ እንደሆነ አቅጣጫ እንዲሰጠኝ እጠይቃለሁ?
  • አልገባኝም? 
  • በርከት ያሉ ኮሚቴዎችን በሰብሳቢነት እንድመራ የተመደብኩ በመሆኑ መምታታት ከመፈጠሩ በፊት ግልጽ ለመሆን ነው፡፡
  • የዋጋ ንረቱ ያመጣብንን ጫና በተመለከተ አይደለም እንዴ እስካሁን ስንነጋገር የነበረው? በሐሳብ ሌላ ጉዳይ ላይ ነበርክ?
  • ይቅርታ ይደረግልኝ ክቡር ሚኒስትር፣ አሁን ማብራሪያውን ለማቅረብ ዝግጁ ነኝ። 
  • መቀጠል ትችላለህ።
  • አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። እንደሚታወቀው ይህ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ያደረገው በተቋቋመ በማግስቱ ነው።
  • ማሳሰቢያ! 
  • አቤት ክቡር ሚኒስትር?
  • የተለመዱ የማብራሪያ መግቢያና መውጫዎችን በመተው ጉዳዩ ላይ ብታተኩር?
  • ጥሩ። ክቡር ሚኒስትር። ኮሚቴው ሥራውን ከመጀመሩ በፊት በቅድሚያ ለማየት የሞከረው በዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ጫና የገጠመውን አካል መለየትና ይህ ጫና የወደቀበት አካል የማቃለያ መፍትሔዎችን በቅድሚያ እንዲያገኝ ማድረግ ነው።
  • በዋጋ ንረት ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚገኘው የከተማው ማኅበረሰብ ክፍል እንደሆነ ያታወቃል፡፡ ይህንን ለመለየት ጥናት ያስፈልጋል እንዴ?
  • ክቡር ሚኒስትር ችግሩን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ያደረግነው ጥናት ያመላከተን በዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ጫና የወደቀበት መንግሥት ነው።
  • ምን? 
  • ክቡር ሚኒስትር ያካሄድነው ሳይንሳዊ ጥናት መንግሥት በዋጋ ንረቱ ከፍተኛ ጫና እንደገጠመው ነው።
  • ስለዚህ ምን ዓይነት የማቅለያ መፍትሔ እንዲወሰድ አደረጋችሁ? 
  • ወደ እሱ እየመጣሁ ነው። 
  • ከመጣህማ ቆየህ!
  • ምን አሉኝ ክቡር ሚኒስትር? 
  • ማብራሪያው ላይ ትዘገያለህ ፈጠን አድርገው እያልኩህ ነው፡፡
  • ጥሩ ክቡር ሚኒስትር። ቀደም ሲል እንዳልኩት የዋጋ ንረቱ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሰ መሆኑን ካረጋገጥን በኋላ ጫናውን ለማቅለል በቅድሚያ የወሰነው የነዳጅ ድጎማ እንዲነሳ ነው።
  • በመቀጠልስ?
  • ቀጣዩ ዕርምጃ ከመወሰናችን በፊት ከድጎማው ጎን ለጎን የብር የመግዛት አቅም እንዲቀንስ ተወስኖ ተግባራዊ እየተደረገ ነው። 
  • በእነዚህ ዕርምጃዎች መንግሥት ላይ የመጣው ጫና እየቀለለ ነው? 
  • መጠነኛ ለውጦች ቢታዩም ጫናው አሁንም መንግሥት ላይ እንደበረታ ነው።
  • ታዲያ ምን ይበጃል አላችሁ? በቀጣይ የምትወስዱት ሌላ የመፍትሔ ዕርምጃ አለ?
  • በትክክል ክቡር ሚኒስትር። ምን ያህል የሚለውን እንጂ የታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ኮሚቴው ወስኗል። 
  • የምን ታሪፍ ጭማሪ?
  • የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ።
  • እህ… ለማኅበረሰቡ በሚቀርበው ኤሌክትሪክ ዋጋ እንዲጨምር ማለትህ ነው?
  • አዎ። 
  • የነዳጅ ድጎማው ቢነሳም የተፈለገውን ያህል ውጤት አላስገኘምና የኤሌክትሪክ ታሪፍ ይጨመር እያላችሁ ነው አይደል?
  • አዎ ክቡር ሚኒስትር። መንግሥት ላይ የወደቀው ጫና ሊገለበጥ የሚችለው በኤሌክትሪክ እንደሆነ ያደረግነው ጥናት ይጠቁማል። 
  • የመንግሥት ጫና ለማቅለል ነው፣ ለመገልበጥ? 
  • ያው ነው ክቡር ሚኒስትር። 
  • ኤሌክትሪክ ነው ያላችሁት አይደል? 
  • ትክክል። ቀጣዩ ዕቅዳችን ኤሌክትሪክ ነው ክቡር ሚኒስትር!
  • ጥሩ ወጥመድ ነው። 
  • የምን ወጥመድ? ክቡር ሚኒስትር? 
  • የኤሌክትሪክ! 
  • እንደዚያ አይደለም ክቡር ሚኒስትር?
  • ያው ነው! 

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከደመወዝ ጭማሪና ከዕርከን ዕድገት ጋር በተያያዘ መንግሥትን አስጠነቀቁ

  ‹‹የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ሳይሆን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንም...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  የአገሪቱ ባንኮች ካፒታል 199.1 ቢሊዮን ብር ደረሰ

  ከታክስ በኋላ 50 ቢሊዮን ብር ማትረፋቸውን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ የአገሪቱ...

  በዓለም ጂኦ ፖለቲካ መድረክ የኢትዮጵያ ተፈላጊነት

  የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በሦስት የአፍሪካ አገሮች...

  በአገር ጉዳይ አንዱ ባለቤት ሌላው ባይተዋር መሆኑ ይብቃ!

  ኢትዮጵያ የታፈረችና የተከበረች አፍሪካዊት አገር ናት፡፡ ለመላው የዓለም ጥቁር...

  ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2015 የሒሳብ ዓመት ተቀማጭ ገንዘቡን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ለማሳደግ እንደሚሠራ አስታወቀ

  በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በተለያዩ ክንውኖቹ ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚመሩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ አጀንዳ አድርጎ በያዘው ወቅታዊ የፀጥታና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ቢጀመርም በስተመጨረሻ አጀንዳውን ስቶ ስለ መዋደድ እየተጨቃጨቀ...

  በዛሬው መደበኛው መድረካችን አጀንዳ የተለመደው የፀጥታና ደኅንነት ጉዳይ ይሆናል። ሌላ አጀንዳ የምታስይዙት አጀንዳ ከሌለ በቀር ማለቴ ነው። ክቡር ሚኒስትር... እሺ ...ቀጥል አመሰግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። መደበኛ አጀንዳው እንደተጠበቀ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ አልቻለም ተብሎ መወቀሱ አልተዋጠልኝም እያሉ ከፖለቲካ አማካሪያቸው ጋር እየተወያዩ ነው]

  እንዴት መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት ማስጠበቅ አልቻለም ይባላል? መንግሥት ስንት ነገር እያደረገ እንዴት ይወቀሳል? እንዴት ክቡር ሚኒስትር?  አንተም ጥያቄ አለህ? ለመወያየት እንጂ እንዳሰቡት አይደለም ክቡር ሚኒስትር። እንዴት እንዲህ አልክ?  ለማለት...