Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ፀረ ኤችአይቪ ኤድስ ጥምረት ፕሬዚዳንት...

  ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ፀረ ኤችአይቪ ኤድስ ጥምረት ፕሬዚዳንት ሆኑ

  ቀን:

  የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ፀረ ኤችአይቪ ኤድስ ጥምረት ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ተስፋዬን የጥምረቱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ፡፡

  በአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ ሰኔ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው 19ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በተካሔደው የአመራር ምርጫ ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ድርጅቱን እ.ኤ.አ. ከ2017 – 2019 ድረስ በፕሬዚዳንትነት የመረጣቸው በአብላጫ ድምፅ ነው፡፡ የቡርኪና ፋሶ ቀዳማዊት እመቤት አጆቪ ሲካ ካቦሬ ደግሞ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ተመርጠዋል፡፡

  ጥምረቱ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች በየአገሮቻቸው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙርያ በተለይም የሴቶችን፣ ሕፃናትንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለሚተገብሩዋቸው ሥራዎች የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግ ነው፡፡

  በድርጅቱ ስትራቴጂ ትኩረት የተሰጣቸው የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች የትኩረት መስኮች ውስጥ የኤችአይቪ ኤድስን ሥርጭት መቆጣጠርና መግታት፣ የእናቶችና ሕፃናትን ጤና ማሻሻል፣ እንዲሁም የወጣቶች የሥነ ፆታና የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ማስፋፋት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

  ቀዳማዊት እመቤት ሮማን፣ የአፍሪካ ቀዳማውያት እመቤቶች ፀረ ካንሰር ኅብረትንም በሊቀመንበርነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...