Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊንግድ ባንክ በሠንጋ ተራ የተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ተረከበ

  ንግድ ባንክ በሠንጋ ተራ የተገነቡ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ተረከበ

  ቀን:

  • ለተመዝጋቢዎች የሚተላለፉት ቤቶች ብዛት 972 መሆናቸው ተጠቆመ

  ከ2007 ዓ.ም. መገባደጃ ጀምሮ በቅርቡ እንደየአከፋፈላቸው ይተላለፋሉ እየባለ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተመዝጋቢውን ግራ ሲያጋቡ ከነበሩት የክራውንና ሠንጋ ተራ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠንጋ ተራዎችን ሙሉ በሙሉ መረከቡ ታወቀ፡፡

  በአምስት ብሎኮች የተገነቡ በእያንዳንዱ ብሎክ 60፣ በድምሩ 300 ቤቶች  የግንባታው ባለቤት ከሆነው የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ጋር በመነጋገርና አንዳንድ ያልተጠናቀቁ ነገሮችን ለማጠናቀቅ በመፈራረም መረከቡን፣ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  ኢንተርፕራይዙ በክራውን ሳይት ካሉት 14 ብሎኮች ውስጥ ሰባቱን ማስረከቡን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ የክራውን ሳይት እያንዳንዱ ብሎክ 48 ቤቶችን እንደያዙ የገለጹት ኃላፊው፣ በድምሩ 336 ቤቶችን በተመሳሳይ ሁኔታ ማስረከቡን አስረድተዋል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ያጠናቀቃቸውን ብሎኮች በየቀኑ እያስረከበ መሆኑን ጠቁመው፣ ሙሉ በሙሉ አስረክቦ የሚጨርስበትን ቀን መገመት ባይቻልም በቅርቡ ይጠናቀቃል የሚል እምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

  ምናልባት በሰኔ ወር መጨረሻ ወይም በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ ለተመዝጋቢዎች ይተላለፋሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ግምታቸውን የተናገሩት ኃላፊው፣ በሁለቱም ሳይቶች ያሉት በድምሩ 972 ቤቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በሠንጋ ተራና በክራውን ሳይቶች በአጠቃላይ 1,292 መኖሪያ ቤቶች እንደሚተላለፉ ሲነገር ቆይቶ እንዴት 972 ብቻ ይሆናሉ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ኃላፊው፣ በሁለቱም ሳይቶች የሚገኙ 320 የንግድ ቤቶች በመሆናቸው ባንኩ እንደማይመለከተው ገልጸዋል፡፡

  በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጠቅላላ ተመዝጋቢዎች ቁጥር ከ164 ሺሕ በላይ ቢሆንም፣ 150 ሺሕ ያህሉ ሳያቋርጡ እየቆጠቡ መሆናቸው ታውቋል፡፡፡ ከ16,000 በላይ የሚሆኑት መቶ በመቶ የከፈሉ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ከ60 በመቶ በላይ የቆጠቡ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ 39,229 የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡ ግንባታቸው የተጠናቀቀው ሁለቱ ሳይቶች (972 ቤቶች) ለተመዘጋቢዎቹ ማለትም ቀደም ብለው መቶ በመቶ ለከፈሉት 2,200 ተመዝጋቢዎች (የኢንተርፕራይዙ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለመገናኛ ብዙኃን በገለጹት መሠረት) መቼ እንደሚተላለፉ አልታወቀም፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ አሻሽሎ ባወጣው የአዲስ አበባ ከተማ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 23(1ረ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ በደንብ ቁጥር 45/2004 የተቋቋመው የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ኃላፊዎች፣ ስለቤቶቹ ግንባታና የክራውን ሳይት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለንግድ ባንክ መቼ እንደሚተላለፍ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሪፖርተር ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም አልተሳካም፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...