Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኦሊምፒክ ዝግጅት የስፖርት ዲፕሎማሲ ሥራዎች አጋርነቱን አረጋገጠ

  ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኦሊምፒክ ዝግጅት የስፖርት ዲፕሎማሲ ሥራዎች አጋርነቱን አረጋገጠ

  ቀን:

  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስፖርቱ ለዜጎች ከሚያበረክተው ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳው ጎን ለጎን በዲፕሎማሲው ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወት ይችል ዘንድ ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጋር ውይይት ማድረጉ ተገለጸ፡፡ የውይይቱ መነሻ ሐሳብም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለ2020 ኦሊምፒክ ከያዘው የአራት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ውስጥ እንዲካተትና ዝግጅቱም ከወዲሁ መጀመር እንዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷልም ተብሏል፡፡

  የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴውን ኃላፊነት በቅርቡ የተረከበው አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኢትዮጵያ በ2020 ኦሊምፒክ በሚኖራት ተሳትፎና እስከዚያው ድረስ መደረግ ስለሚገባው ዝግጅትና እንቅስቃሴ ዙሪያ ሦስት ክልሎችን ማለትም የትግራይ፣ የአማራና የደቡብ ክልሎች ከስፖርቱ መሠረተ ልማት ጀምሮ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የመስክ ምልከታ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

  ስፖርቱ በተለይም በአሁኑ ወቅት ለአገሮች እያበረከተ ካለው ፋይዳ በመነሳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አዲሱን አመራር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውና በውይይቱም ስፖርቱ በዲፕሎማሲው ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ መሥሪያ ቤቱና ኦሊምፒክ ኮሚቴው ተናበው ሊሠሩ ይገባል ማለታቸው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

  እንደ መግለጫው ከሆነ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) የመላ አፍሪካ ጨዋታዎችና የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች እንዲሁም የሌሎችም ውድድሮች ዓላማው በዋናነት፣ 2020 ኦሊምፒክ ላይ የአገሪቱን መልካም ገጽታ የሚገነቡ ተተኪ ወጣት አትሌቶችን ማፍራት ሊሆን እንደሚገባ ለዚህ ስኬት ደግሞ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር መሥራት ለነገ ሊባል እንደማይገባ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

  ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. በሁለቱ ተቋማት መካከል በተደረገው ውይይት የኦሊምፒክ ጉዳይ የአገር ጉዳይ ከመሆኑም ባሻገር የዓለም አገሮችን በጋራ የሚያስተሳስር ስፖርታዊ ቋንቋ ስለመሆኑ ጭምር መግባባት ላይ መድረሳቸው ታውቋል፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተልዕኮን ማገዝ ብቻ ሳይሆን ቋሚ ግንኙነት ፈጥሮ አብሮ መሥራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

  ለእያንዳንዱ አትሌትም ሆነ የስፖርት አመራር ለዚህ ዕቅድ ዕውን መሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሕግ ማዕቀፍና ከሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲ ምንነትና ፋይዳ አኳያ ሥልጠናዎች እንዲሰጥ ፕሬዚዳንቱ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ሚኒስትሩም  አዎንታዊ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...