Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ ማከፋፊያ ቀመር አፀደቀ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ ማከፋፊያ ቀመር አፀደቀ

  ቀን:

  • ሦስት ክልሎች ትልቅ ድርሻ ይኖራቸዋል

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል አዲስ የድጎማ በጀት ማከፋፊያ ቀመር አፀደቀ፡፡

  ምክር ቤቱ ሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባዔ በአጀንዳነት ከያዛቸው ጉዳዮች መካከል የክልሎች ድጎማ በጀት ማስፋፊያ ቀመር አንዱ ነበር፡፡

  የምክር ቤቱ የበጀት ድጎማና የጋራ ገቢዎች ድልድል ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የክልሎችን የወጪ ፍላጎትና ገቢ የማመንጨት አቅም (Potential) መሠረት አድርጎ ረቂቅ ቀመሩን አሰናድቶ ለምክር ቤት አቅርቧል፡፡ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገብሩ ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ቀመሩን ለማዘጋጀት በመረጃነት ከተወሰዱት የወጪ ፍላጎት መመዘኛዎች ዋነኞቹ ተጠቅሰዋል፡፡

  እነዚህም ለሥራ አመራርና ጠቅላላ አገልግሎት፣ ለጤና፣ ለውኃ፣ ለከተማ ልማት፣ ለትምህርት፣ ለገጠር ልማትና ለመሳሰሉት የወጪ ፍላጎቶች ናቸው ብለዋል፡፡

  በሌላ በኩል የክልሎች ገቢ የማመንጨት አቅም ሌላው መመዘኛ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ገብሩ፣ እነዚህም የገቢ ግብር፣ የሠራተኛ ደመወዝ፣ የመሬት መጠቀሚያ ክፍያ፣ ተርን ኦቨር ታክስና ቫት መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ ሁለቱን ማለትም የወጪ ፍላጎትና ገቢ የማመንጨት አቅም በማጣጣም ጉድለቱን ለመሙላት እንዲያመች ተደርጎ ቀመሩ መዘጋጀቱን፣ ሕጋዊ አሠራሩም ይህ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

  በዚህም መሠረት ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚበጅተው ገንዘብ በአዱሱ ቀመር እንደሚከፋፈል ጠቁመዋል፡፡

  በቀመሩ መሠረት ኦሮሚያ ክልል 34.46 በመቶ፣ አማራ ክልል 21.6 በመቶ፣ ደቡብ ክልል 20.11 በመቶ በማግኘት ከአንድ እስከ ሦስት ደረጃ ይዘዋል፡፡

  በመቀጠል ሶማሊያ ክልል 9.98 በመቶ፣ ትግራይ ክልል 6.03 በመቶ፣ አፋር ክልል 3.02 በመቶ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል 1.8 በመቶ፣ ጋምቤላ ክልል 1.33 በመቶ፣ ድሬዳዋ አስተዳደር 0.88 በመቶ፣ ሐረር ክልል 0.76 በመቶ ይገኛሉ፡፡

  ድሬዳዋ የፌዴራል መንግሥት ከተማ እንጂ ክልል ባለመሆኗ ለረዥም ጊዜ የበጀት ድጎማ ሳታገኝ የቆየች ቢሆንም፣ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን እንድታገኝ ፖለቲካዊ መፍትሔ ተሰጥቷል፡፡

  በዚህ ቀመር ላይ አንዳንድ ክልሎች ቅሬቸውን ያሰሙ ሲሆን፣ በተለይ ትግራይ ክልል የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ቀመሩ ከግምት እንዳላስገባና ወደፊት ሊስተካከል እንደሚገባው የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ ተከራክረዋል፡፡

  ትልልቆቹ ክልሎች በበኩላቸው ከቀድሞው ያነሰ ድጎማ እንዲያገኙ የሚያደርጋቸው እንደሆነ በመግለጽ ተከራክረዋል፡፡

  ይሁን እንጂ የድጎማ በጀት ዋናው ዓላማ የተመጣጠነ የክልሎች ዕድገት ለማምጣት የታለመ መሆኑ ተብራርቶ ቀመሩ እንዲፀድቅ ተወስኗል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...