Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአራት የኦሮሞ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ድርድር የሚገኘውን ውጤት...

  አራት የኦሮሞ ፓርቲዎች ኢሕአዴግ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ድርድር የሚገኘውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታወቁ

  ቀን:

  • ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያቀረበውን ሪፖርት ተቃውመዋል

  የኦሮሞ ኦቦ ነፃነት ግንባር (ኦአነግ)፣ የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር (ኦነአግ)፣ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) እና የኦሮሚያ ነፃነት ብሔራዊ ፓርቲ (ኦነብፓ)፣ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሚያደርገው ድርድር የሚገኘውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡

  ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ አገር አቀፍና የአካባቢ ምርጫዎች ላይ በመሳተፍ ብቻ ሳይሆን ‹‹ምርጫ ቦርድ በየጊዜው አሸናፊነቱን ለሚያበስርለት ኢሕአዴግ›› ቅድሚያ ድጋፍ በመስጠት፣ የድኅረ ምርጫ ሰላማዊ ሒደት እንዲቀጥል የበኩላቸውን ሚና ሲጫወቱ ቆይተዋል፡፡ ያንን የሚያደርጉት የገዢውን ፓርቲ ትኩረት ለመሳብ ወይም ልዩ ጥቅም ለማግኘት አይደለም ብለዋል፡፡ ምርጫዎቹም ዴሞክራሲያዊ ሆነው ሳይሆን ‹‹እያወቅሁ ከነምናምኑ›› እንዳለችው የቤት እንስሳ መጪው ጊዜ የተሻለ እንደሚሆን በማሰብ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

  ስለፓርቲዎች ድርድር፣ የኦሮሚያና የሶማሌ ክልሎች ግጭትና የኦሮሞ ሕዝብ ከፊንፊኔ ማግኘት የሚገባውን ልዩ ጥቅም በሚመለከት ፓርቲዎቹ በጎ የመሰላቸውን ሐሳብ ሲሰነዝሩ መቆየታቸውንም አስታውሰዋል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ፓርቲዎቹ አጠቃላይ ሁኔታውን ሲመለከቱ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄና የእነሱ ጩኸት ሰሚ ጆሮ ተነፍጓቸው፣ ነገሮች ሁሉ በባሰ ሁኔታ እየገሰገሱ መሆናቸውን እየተመለከቱ በመሆናቸው፣ ኢሕአዴግና አገር አቀፍ ፓርቲዎች እያደረጉት ያሉት ድርድር የኦሮሞን ሕዝብ ችግር ፈትቶ የሕዝብን መብት ያስከብራል የሚል እምነት ስለሌላቸው፣ ውጤቱ ምንም ይሁን ምንም የማይቀበሉት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

  ሌላው ፓርቲዎቹ ያነሷቸው ነጥቦች ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባለፈው ዓመት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች፣ እንዲሁም በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን የተከሰተውን፣ በሕዝብ ተቃውሞ ሳቢያ የተፈጸመውን እልቂት በሚመለከት፣ ኮሚሽነሩ  አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር (ዶ/ር) ያቀረቡትን ሪፖርት ተቃውመዋል፡፡

  በተለይ በኦሮሚያ ክልል በሕዝብ ላይ የተፈጸመው ግድያ ተመጣጣኝ መሆኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት ከሀቅ የራቀ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹ሪፖርት አቅራቢው ያቀረቡት ሪፖርት ገለልተኛ አካል ያጣራው ነው የሚል እምነት የለንም፤›› ብለዋል፡፡

  መንግሥት ከኃላፊነት ለመሸሽ የሚያደርገውን ሩጫ ትቶ በዓለም አቀፍ ገለልተኛ ወገኖች እንዲጣራና ለሞቱና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ጠይቀዋል፡፡ ተመጣጣኝ ያልሆነ ጉዳት ያደረሱትን የፀጥታ ኃይሎችና ዕርምጃውን እንዲወስዱ ትዕዛዝ የሰጡ ኃላፊዎችን መንግሥት ለሕግ እንዲያቀርባቸው፣ መንግሥት ደግሞ ሕዝብንም ይቅርታ እንዲጠይቅ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...