Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  በአዲስ አበባ በጅምር የቀሩ ሕንፃዎች እየተበራከቱ ነው

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በአዲስ አበባ ከተማ ለረዥም ዓመታት ታጥረው ከተቀመጡ ቦታዎች በተጨማሪ፣ ግንባታቸው ቢጀመርም ሳይጠናቀቁ ቆመው የቀሩ ሕንፃዎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡

  በአዲስ አበባ ከተማ በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች በጅምር የቀሩ በርካታ ሕንፃዎች ማየት እየተለመደ ሲሆን፣ አስተዳደሩ ዕርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ነዋሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ቅሬታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

  የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜን ይደነግጋል፡፡

  አዋጁን ለማስፈጸም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያወጣው ደንብ ቁጥር 49/2004 ቦታ በሊዝ የተፈቀደለት አካል የሊዝ ውል ተፈራርሞ፣ የግንባታ ፈቃድ ከወሰደበት ቀን አንስቶ በተቀመጠው የጊዜ ጣሪያ ግንባታው በማጠናቀቅ በቦታው ላይ አገልግሎት መጀመር እንዳለበት ይደነግጋል፡፡

  በደንቡ ላይ እንደተገለጸው ለአነስተኛ ደረጃ ግንባታዎች 24 ወራት፣ ለመካከለኛ ደረጃ ግንባታዎች 36 ወራት፣ ለከፍተኛ ግንባታዎች 48 ወራት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተሰጥቷል፡፡

  በዚህ ሒደት ማለፍ ያልቻሉ ፕሮጀክቶች እንደሚያቀርቡት ምክንያት ማራዘሚያ የሚሰጥ ሲሆን፣ ማራዘሚያውም ከስድስት እስከ 12 ወራት ብቻ ነው፡፡

  ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ሕንፃዎች ግንባታቸው ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ ከአሥር ዓመት በላይ ቆመው የቀሩ፣ ይሰጣሉ የተባለውም አገልግሎት የውኃ ሽታ ሆኖ የቀረ እጅግ በርካታ ናቸው፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት ማኔጅመንትም ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በተሰጣቸው ኃላፊነት መሠረት የሕዝብ ሀብት በፈሰሰባቸው ግንባታዎች ላይ ቁጥጥር አለማድረጋቸው ቅሬታ እየፈጠረ ነው፡፡

  ከእነዚህ ቆመው ከቀሩ ሕንፃዎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ቦታዎች ለዓመታት ታጥረው ይገኛሉ፡፡

  የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በ2009 በጀት ዓመት 20 ሺሕ የሊዝ ቦታዎች ላይ ቁጥጥር ማድረጉ፣ በተለያየ ምክንያቶች በወቅቱ ግንባታ ማካሄድ ላልቻሉ 4,600 ቦታዎች የሊዝ ውል ማሻሻያ ማድረጉ፣ ለ2,044 ፕሮጀክቶች ደግሞ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አመልክቷል፡፡

  ነገር ግን ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ 138 ቦታዎች ከመስከረም 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ ግንባታ ካልጀመሩ ዕርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል፡፡

  ከእነዚህ ቦታዎች ውስጥ 24 ያህሉ የመንግሥት፣ ስምንት የሚጠጉ ቦታዎች ደግሞ የሚድሮክ ናቸው፡፡

   

   

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች