Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናወታደራዊ ካምፖችንና የመንግሥትን ተቋማት ለማውደም ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

  ወታደራዊ ካምፖችንና የመንግሥትን ተቋማት ለማውደም ሲንቀሳቀሱ ተይዘዋል የተባሉ ግለሰቦች ተከሰሱ

  ቀን:

  ከወታደሮች ካምፕ የጦር መሣሪያ በመዝረፍና በጦር መሣሪያ የተደገፈ አመፅ ለማካሄድ በማሰብ አዋሽ ሦስተኛ፣ አራተኛ፣ አምስተኛ፣ ስድስተኛና ሰባተኛ የሚገኙ የጦር ካምፖችን ለማውደም በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉ ሦስት ግለሰቦች፣ ሰኞ መጋቢት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው፣ ተከሳሾቹ በሰኔ ወር መጨረሻ 2008 ዓ.ም. የኦነግ ከፍተኛ አመራር ናቸው ከተባሉት ከአቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በዋትስአፕ በመጠቀም ይገናኙ ነበር፡፡ በመንግሥት ተቋማት ላይ ዕርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው፣ በኦሮሚያ የሚገኙ ባለሀብቶችን በማስተባበር ለኦነግ ታጣቂዎች ጠመንጃና ጥይት እንዲገዙ ማድረግ እንዳለባቸው ተልዕኮ ተሰጥቷቸው እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

   በ2008 ዓ.ም. በኦሮሚያ ከተካሄዱት ረብሻዎችና አመፆች መካከል በአዳማ ከተማ የሚካሄደውን የአመፅ ሰልፍ እንዲመሩ፣ በአካባቢው የሚገኙ ሚሊሻዎችን መንግሥት ያስታጠቃቸውን ጠብመንጃዎች በመንጠቅ ለኦነግ ታጣቂዎች እንዲሰጡም ትዕዛዝ ተላልፎላቸው እንደነበር አክሏል፡፡

  ተከሳሾቹ መሀዲ አሊይ ገዳ፣ አህመድ አደምና ዓሊ ድልቤቶ ይባላሉ፡፡ ሦስቱም በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ውስጥ ነዋሪ መሆናቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ ተከሳሾቹ ከ2002 ዓ.ም. ጀምሮ በኦነግ ውስጥ አባል ለመሆን ተመልምለው፣ የተለያዩ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠናዎችን መውሰዳቸውም በክሱ ጠቁሟል፡፡ ከባሌ ዞን ጎባ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘውና ሰናቴ ተብሎ በሚጠራው ጫካ ውስጥ የኦሮሞ ታሪክ፣ የኦነግ ድርጅት ዓላማ፣ የኦነግ ሕገ መንግሥት፣ የኦነግ ድርጅት ሥነ ሥርዓትና ሥነ ምግባር፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በፖለቲካ ውስጥ ያለውን ሚና በሚገልጹ አምስት ርዕሶች በድርጅቱ አመራሮች አማካይነት ለዘጠና ቀናት ሥልጠና መውሰዳቸውንም ዓቃቤ ሕግ አስረድቷል፡፡

  ተከሳሾቹ በኦሮሚያ ክልል የክረምት ትምህርት አርባ ምንጭና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ መምህራን ትምህርት እንዳይጀምሩ መደረጉን፣ በአሜሪካ ራዲዮ ድምፅ የሐሰት ወሬ ማስተላለፋቸውንም ክሱ ይጠቁማል፡፡ የኦነግ ከፍተኛ አመራር ናቸው ከተባሉት አቶ ጃዋር መሐመድ ጋር በተደጋጋሚ በዋትስአፕ በመገናኘት ተልዕኮ ይሰጣቸው እንደነበር የሚገልጸው ዓቃቤ ሕግ፣ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምን ያህል የሕግ ታራሚዎች እንደተጎዱ እንዲያጣሩ፣ የጦር መሣሪያ በመጠቀም መንገድ እንዲዘጉ፣ በመንግሥት ተሸከርካሪዎች ላይ ዕርምጃ እንዲወስዱና መንግሥታዊ ተቋማትን እንዲያወድሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው እንደነበረም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡

  ከጳጉሜን 1 ቀን 2008 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2 ቀን 2009 ዓ.ም. ድረስ የንግድ ተቋማት እንዳይከፈቱ፣ ከፍተው በሚገኝ አካላት ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድና እነርሱም የኦሮሞ ጠላት ተብለው እንዲፈረጁ፣ ግብር እንዳይከፍሉ፣ በመንግሥት ስብሰባ ላይ እንዳይሳተፉ የሚገልጽ ጽሑፍ እንዲያሠራጩ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸውም ክሱ ያብራራል፡፡

  ሌላው የኦነግ አባል መሆኑን ገልጾ ዓቃቤ ሕግ መጋቢት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ የመሠረተበት ተከሳሽ መሠረት አስፋው አብዲሳ ይባላል፡፡ ተከሳሹ ‹‹መሠረት ጂሜል ዶት ኮም›› በሚባል ማኅበራዊ ድረ ገጽ በመጠቀም ለኦነግ አባላትን በመመልመል፣ በማደራጀትና በድረ ገጹ ሲያስተላልፍና ሼር ሲያደርግ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡

  የኦነግ አመራር መሆናቸው ከተገለጸው አቶ ጃዋር መሐመድ በሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሲሰጡ የነበረውን የሽብር ተልዕኮ ተቀብሎ፣ በአምቦና በአካባቢው የሚገኙ ወጣቶች በሕገወጥ ሠልፍ ላይ እንዲሳተፉ ማድረጉንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ በአምቦና በጊንጪ ከተሞች እንደተደረገው፣ የኦነግ ዓርማን በየመንገዱ ላይ አንፀባራቂ አድርጎ ለመሳል ሁለት ጋሎን ቀለም ቤለማ ጉተ

  ታ ሚልኬሳ ከሚባል የኦነግ አባል መቀበሉንም አክሏል፡፡ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ)ና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 7(1)ን ተላልፈው በመገኘታቸው፣ በፈጸሙት በሽብርተኛ ድርጅት ውስጥ በማንኛውም መልኩ መሳተፍ ወንጀል ክስ እንደተመሠረተባቸው ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡ 

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

  መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ...

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...