Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበሙስና የተከሰሱት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

  በሙስና የተከሰሱት የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች የእምነት ክህደት ቃል ሰጡ

  ቀን:

  • የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊዎች መቃወሚያቸውን እንዲያቀርቡ ተቀጠሩ

  በሙስናና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን ወ/ሮ ፀዳለ ማሞን ጨምሮ፣ 13 ተከሳሾች ዓርብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

  ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የሙስና ወንጀል ክስ ላይ መቃወሚያ ካላቸው ክሱን ለሚመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ለማቅረብ ቢሆንም፣ ወ/ሮ ፀዳለን ጨምሮ ዘጠኝ ተከሳሾች ‹‹መቃወሚያ የለንም›› ብለዋል፡፡ በመሆኑም የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርገዋል፡፡

  ፍርድ ቤቱ ወ/ሮ ፀዳለ ማሞ፣ አቶ የማነ ፀጋዬ፣ ወ/ሮ ሳባ ገብረ መድኅን፣ አቶ ሽመልስ ዓለማየሁ፣ አቶ የማነ ግርማይ፣ ወ/ሮ ትርሲት ከበደ፣ ወ/ሮ አልማዝ ዓይናለም (በዋስ ናቸው) እና አቶ ወንድሙ መንግሥቱ (በዋስ ናቸው) ‹‹ድርጊቱን ፈጽማችኋል? ጥፋተኞች ናችሁ?›› ብሎ ጠይቋቸው፣ ‹‹ድርጊቱን አልፈጸምንም፣ ጥፋተኞችም አይደለንም፤›› በማለት ተመሳሳይ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

  ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ ክደው በመከራከራቸው፣ ዓቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በተከሶሾቹ ላይ የቀረበባቸው ክስ በሰነድና በሰው ምክስሮች የተረጋገጠ በመሆኑ፣ ምስክሮቹን አቅርቦ እንዲያሰማ እንዲታዘዝለት በመጠየቁ፣ ለጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

  በሌላ በኩል በአምስት የክስ መዝገቦች የሙስና ክስ የተመሠረተባቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዛይድ ወልደ ገብርኤልና ሌሎች የባለሥልጣኑ ኃላፊ ከነበሩ ተከሳሾች የተወሰኑት የክስ መቃወሚያ ያቀረቡ ቢሆንም፣ አቶ ዛይድን ጨምሮ አራት ተከሳሾች ሳያቀርቡ ቀርተዋል፡፡

  ለምን የቅድመ ክስ መቃወሚያ እንዳላቀረቡ ተጠይቀው እንደተናገሩት፣ ክሱ በርካታና ውስብስብ ነው፡፡ በመሆኑም በመደበኛ የክስ ሥርዓት ሕግ ለመቀጠል አስቸጋሪ ስለሆነ፣ የቅድመ ክስ ክርክር እንዲያደርጉ እንዲፈቀድላቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡ ይኼ አካሄድ ለተከሳሾቹ የተፋጠነ ፍትሕ ሊያስገኝ እንደሚችልም ጠቅሰዋል፡፡

  ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ የቅድመ ክስ ክርክርና በመደበኛ ክርክር ሒደት ላይ በተደረገ ጥናት፣ ለተፋጠነ ፍትሕ ጠቃሚ ሆኖ የተገኘው በመደበኛ ሥርዓት ሕግ መቀጠል መሆኑንና ቀደም ብሎ ብይን የተሰጠበት መሆኑን በማስታወስ፣ የተከሳሾች ጠበቆች ያነሱትን ሐሳብ ውድቅ አድርጎታል፡፡ ተከሳሾች በክሱ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች ያልተተረጎሙ፣ ቁጥራቸው ያልተሟላና የማይነበቡ መሆናቸውን ማመልከታቸውን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ዓቃቤ ሕግ ከቀጣይ ቀጠሮ በፊት አሟልቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የማያቀርብ ከሆነ በቀረበው ልክ ብቻ እንደሚያከራክርም አስታውቋል፡፡

  ዓቃቤ ሕግም ያልተተረጎሙትን ማስረጃዎች እንደሚያስተረጉምና ያልተሟሉትን እንደሚያሟላ ስለገለጸ፣ የተከሰሾቹን የክስ መቃወሚያ ለመጠባበቅ ለጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

  የፌዴራል ፖሊስ በሌሉበት የተከሰሱትን አፈላልጎ እንዲያቀርብና ቀደም ብሎ የታዘዘውን ለምን እንዳልፈጸመ ኃላፊዎች በቀኑ ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

   

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

  መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ...

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...