Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትር

  [የጥምቀት በዓል የሚከበርበት ቀን በመሆኑ ክቡር ሚኒስትሩ ቤታቸው ከባለቤታቸው ጋር ናቸው]

  • እንዴት አምሮብሻል እባክሽ?
  • እኔ የአንተ ሚስት አሁንም እኮ ቆንጆ ነኝ፡፡
  • የሐበሻ ቀሚስ ስትለብሺ ደግሞ ውበትሽ በእጅጉ ጨመረ፡፡
  • ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ሲባል አልሰማህም?
  • ወዴት ልትሄጂ ነው ታዲያ?
  • ታቦት ልሸኝ ነዋ፡፡
  • እንዲህ ውብ ሆነሽ?
  • ምነው ፈራህ እንዴ?
  • አንዱ ሎሚ እንዳይወረውርብሽ ብዬ ነው፡፡
  • ሎሚ እኮ ድሮ ቀረ፡፡
  • ታዲያ ምንድን ነው የሚወረወረው?
  • የቪትዝ ቁልፍ ነዋ፡፡
  • የጥምቀት ስጦታ በእጅጉ ተመንድጓላ?
  • እንደ አገራችን ዕድገት በ11 በመቶ ብቻ ያደገ መስሎህ ነበር?
  • እስቲ አሽሙርሽን ተይው፡፡
  • ተነስተህ ታቦት እንሸኝ እንጂ?
  • እኔ እባክሽ ከቤት አልወጣም፡፡
  • ምን ታደርጋለህ?
  • ቁጭ ብዬ ዜና እከታተላለሁ፡፡
  • እሺ ቢያንስ ነጭ ልብስ እንኳን ልበስ፡፡
  • አሁን ነጭ ልብስ መልበስ አይቻልም፡፡
  • ለጥምቀት ካልለበሰ መቼ ልትለብስ ነው ታዲያ?
  • እኔ ነጭ ልብስ የምለብሰው…
  • መቼ ነው?
  • የባቡር መንገዳችን ሲያልቅ፡፡
  • እ…
  • የህዳሴ ግድባችን ሲጠናቀቅ፡፡
  • እሺ፡፡
  • ቀጣዩን ምርጫ ስናሸንፍ፡፡
  • ሌላስ?
  • መልካም አስተዳደር በአገሪቱ ሲሰፍን፡፡
  • እሺ፡፡
  • ድህነት ከታሪካችን ሲወገድ፡፡
  • ወገኛ ነህ፡፡
  • ያኔ ነው እኔ ነጭ ልብስ የምለብሰው፡፡
  • ምኞትህን ያሳካልህ፡፡
  • ይህ ምኞት ሳይሆን ህልሜ ነው፡፡
  • እሺ፣ ህልምህ እውን ይሁንልህ፡፡
  • አሜን፡፡
  • ግን ጠንክሮ መሥራቱን አትዘንጋው፡፡
  • እንግዲህ እንደምታይኝ ነው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • እንቅልፍ እኮ የለኝም፡፡
  • እሱማ እንቅልፍ እንቢ ብሎህ ነው፡፡
  • እንቅልፍ እንቢ ያለኝ በአገሬ ምክንያት ነው፡፡
  • እንዴት?
  • በዚህ ጋ ግድቡ፣ በዚህ ጋ ባቡሩ እያሉ እንቅልፍ ከየት ይመጣል?
  • እኔ የምለው አንተ ባቡር ሐዲድ ላይ አትተኛ?
  • እ…
  • ወይስ ሳላውቀው ግድቡ ላይ ማደር ጀምረሃል?
  • ምን እያልሽ ነው?
  • አይ ባቡርና ግድብ ስትለኝ ከእንቅልፍ ጋር ምን አገናኘው ብዬ ነው?
  • እንዴት አይገናኝ?
  • እኮ አስረዳኝ?
  • እነዚህ ፕሮጀክቶች እኮ ሕዝቡ በጉጉት የሚጠብቃቸው ናቸው፡፡
  • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
  • ታዲያ ካወቅሽ ለምን ትጠይቂኛለሽ?
  • እኔ ያልኩት ከአንተ እንቅልፍ ጋር ምን አገናኘው?
  • ፕሮጀክቶቹ ሳያልቁ መተኛት አልችልም፡፡
  • ለጥሩ እንቅልፍ መድኃኒቱ ጥሩ ህሊና ነው እባክህ?
  • ምን እያልሽ ነው?
  • ምን አልኩ?
  • ጥሩ ህሊና የለህም እያልሽኝ ነው?
  • አልወጣኝም፡፡
  • በይ እስቲ ታቦትሽን ሸኝተሽ ነይ፡፡
  • በል ቻው፡፡
  • ቻው፡፡

  [የክቡር ሚኒስትሩ ወዳጅ የሆኑ ሌላ ሚኒስትር ደወሉላቸው]

  • ጤና ይስጥልኝ፡፡
  • እንኳን አደረስዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንኳን አደረሰህ፡፡
  • በዓሉ እንዴት ነው፡፡
  • ልማታዊ በዓል ነው፡፡
  • ልማታዊ ሲሉኝ?
  • ያው ቤቴ ሆኜ እየተዝናናሁ ነኝ፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር ምን ነካዎት?
  • ምን አጠፋሁ?
  • አሁን እኮ የምንዝናናበት ጊዜ አይደለም፡፡
  • ዛሬ የዕረፍት ቀን ነው እኮ?
  • ቢሆንም ለእኛ የዕረፍታችን ቀን አይደለም፡፡
  • እሱማ ልክ ነህ፡፡
  • ከፊታችን እኮ እጅግ ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎብናል፡፡
  • እሱማ እኔም ደፋ ቀና እያልኩ ነው፡፡
  • የጂቲፒ ሁለት ሥራ በፍጥነት እንዲጠናቀቅ ተብሏል፡፡
  • መቼ?
  • አሁን የደወልኩት እኮ እርስዎ የሚመሩትን ኮሚቴ ምክረ ሐሳብ ከነገወዲያ እንዲያስገቡ ልነግርዎት ነው፡፡
  • ምን?
  • አዎ ጂቲፒ ሁለት በአፋጣኝ መጠናቀቅ አለበት ተብሏል፡፡
  • እኔ እኮ የሚገርመኝ በየኮሪደሩ እየወሰናችሁ እኛን ለምን ታስጨንቁናላችሁ?
  • ክቡር ሚኒስትር ከላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡
  • ከላይ ከመጣማ ምን ይደረጋል?
  • ስለዚህ በአፋጣኝ ተጠናቆ ይድረስ፡፡
  • በቃ እሺ እሞክራለሁ፡፡
  • ለሙከራ ጊዜ የለንም፡፡
  • እ…
  • ከነገወዲያ እንገናኝ፡፡
  • እሺ፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸው ዘንድ ደወሉ]

  • እንኳን አደረስዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንኳን አደረሰህ፤ የምን ጫጫታ ነው የሚሰማኝ?
  • ታቦት እየሸኘሁ ነው፡፡
  • ምን አልከኝ?
  • ታቦት እየሸኘሁ ነኝ፡፡
  • ታቦት?
  • አዎ ምነው?
  • የደላው ሙቅ ያኝካል አሉ፡፡
  • ምን አጠፋሁ ክቡር ሚኒስትር?
  • ስንት ሥራ ተከምሮብን አንተ ትዝናናለህ?
  • የምን ሥራ?
  • የጂቲፒ ሁለት ፕላን በአፋጣኝ ይፈለጋል፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው፡፡
  • የአገር ፕላን እኮ እንዲህ በቀላሉ አይሠራም፡፡
  • ምንም አማራጭ የለንም፡፡ ፕላኑ ከነገወዲያ ይፈለጋል፡፡
  • በቃ ቢሮ እንገናኝ፡፡
  • እሺ በአፋጣኝ ና፡፡

  [የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሯቸው እየጠበቃቸው ነው]

  • ቆየሁብህ አይደል?
  • አይ መንገዱ ሊዘጋጋ እንደሚችል ገምቼያለሁ፡፡
  • አንተ እንዴት ቶሎ ደረስክ?
  • እዚሁ አካባቢ ስለነበርኩ ነው፡፡
  • በል ማስታወሻ ያዝ፡፡
  • የምን ማስታወሻ?
  • የፕላኑን ዋና ሐሳቦች ልንገርሃ?
  • ሁሉም እዚህ ፍላሽ ዲስክ ውስጥ አለልዎት፡፡
  • የአገር ፕላን የሚያህል ነገር እዚች ፍላሽ ዲስክ ውስጥ?
  • 64 ጂቢ ፍላሽ ዲስክ ነው፡፡
  • አንተ እኮ ጀግና ነህ፡፡
  • ራምዎት ግን 32 ኬቢ ነው ልበል?
  • ምን አልከኝ?
  • ሁሉም ነገር እዚህ ውስጥ አለልዎት፡፡
  • ስለዚህ እኔ ማየት አይጠበቅብኝም?
  • አያስቡ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በቃ አመሰግናለሁ፤ ነገ እንገናኝ፡፡
  • መልካም በዓል፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ ቤታቸው ሲመለሱ ከባለቤታቸው ጋር ተገናኙ]

  • ሸኝተሽ መጣሽ?
  • በጣም ደስ የሚል በዓል ነበር፡፡
  • እንዴት?
  • በቃ ኢትዮጵያ በባህል ሀብታም አገር መሆኗን የሚያሳይ በዓል ነው፡፡
  • እኔ የምልሽ?
  • አቤት?
  • በግ ገዝተሽ ነው?
  • ኧረ አልገዛሁም፡፡
  • ታዲያ ግቢው ውስጥ ያለው በግ ማን አምጥቶት ነው?
  • አንድ የአንተ ወዳጅ ነው ያመጣው፡፡
  • እውነት?
  • ብቻ ተጠንቀቅ፡፡
  • ከምኑ ነው የምጠነቀቀው?
  • ከእንዲህ ዓይነት ስጦታ፡፡
  • ምን ላድርግ እኔ?
  • እንዴት ምን ላድርግ ስትል?
  • ሰው ይወደኛል፡፡
  • እ…
  • አገሬን እኮ በቅንነት የማገለግል ሰው ስለሆንኩ ነው፡፡
  • እሱ ጥሩ ነው፡፡
  • እንቅልፍ አጥቼ ሌት ተቀን ስለምሠራ ነው፡፡
  • ጥሩ፡፡
  • ታዲያ ሰው ባይወደኝ አይገርምሽም?
  • ቢሆንም?
  • ይኸው ጂቲፒ ሁለት እየቀረፅን ነው፡፡
  • እኔ የምልህ ሰው የሚለውን ሰምተሃል ግን?
  • ምን እየተባለ ነው?
  • የምርጫው ውጤት ተረጋገጠ ወይ እያለ ነው፡፡
  • እንዴት?
  • ከአሁኑ ጂቲፒ ሁለት የምትቀርፁት ምርጫውን አረጋግጣችሁ ነው እየተባለ ነው፡፡
  • ያ ሌላ ይኼ ሌላ፡፡
  • እንዴት?
  • ይህ እኮ የአገር ጉዳይ ነው፡፡
  • ያኛውስ?
  • እሱ የፓርቲ ጉዳይ ነው፡፡
  • አሁን መጀመሪያ ያነሳሁትን ሐሳብ አታረሳሳኝ፡፡
  • የትኛውን?
  • የስጦታውን ጉዳይ፡፡
  • እኮ ምን ላድርግ?
  • ስጦታ አትቀበል?
  • አሁን በግ ምን አላት?
  • በኋላ ለአሽሟጣጭ እንዳትዳርገኝ፡፡
  • እቺ እኮ ትንሽ ስጦታ ናት፡፡
  • የስጦታ ትንሽ የለውም ሲባል አልሰማህም?
  • ታዲያ ስጦታ ሲመጣ እንቢ ይባላል?
  • አዎ?
  • ለምን?
  • ከስጦታው በስተጀርባ ያለው ፍላጎት ኃፍረት ውስጥ ይከታል! ያዋርዳል!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...

  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተጀመረው የድርድር ሒደት አሳታፊ እንዲሆን ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት...

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወዳጃቸው ከሆነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር ሻይ ቡና እያሉ በኬንያ ስለተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተጫወቱ ነው]

  ኬንያ በዚህ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም ነበር ክቡር ሚኒስትር። አዎ። ጥሩ ዝግጅት አድርገውበታል። ቢሆንም... ቢሆንም ምን ክቡር ሚኒስትር?  እባክህ ክቡር ሚኒስትር የምትለውን ነገር አቁም። ወዳጅ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...