Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ሦስት ሠራተኞች ተከሰሱ

  የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ሦስት ሠራተኞች ተከሰሱ

  ቀን:

  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 ውስጥ የሚገኝ በ413 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ባለ አምስት ፎቅ ሕንፃ ላይ የተሰጠ ውክልና የተሻረና በክፍለ ከተማው ተመዝገቦ እያለ፣ የተሰጠው ሕጋዊ ውክልና እንዳልተነሳ አስመስለው ለባንክ ማረጋገጫ በመስጠት ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ ሦስት የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ተከሰሱ፡፡

  ሠራተኞቹ የይዞታ አስተዳደር ኦፊሰር አቶ ዘካርያስ ኃይሉ፣ የሰነዶች ማረጋገጫ ኦፊሰሮች ገነት ጤናውና ምናሴ ዮሐንስ ሲሆኑ፣ የወንጀል ድርጊቱ እንዲፈጸም አድርገዋል የተባሉት ንግሥት ተሾመ የተባሉ ግለሰብም በክሱ ተካተዋል፡፡

  በግል ሥራ ተሰማርተዋል የተባሉት ንግሥት ተሾመ በክፍለ ከተማው በ413 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ የአገልግሎት ድርጅት ባለ አምስት ፎቅ ሕንፃ፣ በእሳቸውና በአቶ ገብረ ማርያም ፍታዊ የተመዘገበ ሲሆን፣ ሕንፃውን ለማስተዳደር ንግሥት ተሾመ በሰነዶች ማረጋገጫ ውክልና መውሰዳቸውን ዓቃቤ ሕግ የመሠረተው ክስ ያስረዳል፡፡

  ነገር ግን አቶ ገብረ ማርያም የሰጡትን ውክልና በማንሳት ለጽሕፈት ቤቱ ያሳወቁ ቢሆንም፣ የንግሥት ተሾመ የጋራ ንብረት የሆነውን ንብረት በባንክ ዕዳ ማስከበሪያነት እንዲታገድላቸው በተሻረ ውክልና ሲጠይቁ፣ ሦስቱም የክፍለ ከተማው መሬት ልማት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ተቀብለው ማስተናገዳቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ ሠራተኞቹ ሕንፃው በተቋሙ በኩል የተመዘገበ መሆኑን ለብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ ገልጸው በመጻፋቸው፣ ግለሰቧ 5,206,790 ብር ብድር እንዲያገኙ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቶ ጽፏል፡፡

   በመሆኑም ግለሰቧ ያላግባብ ከባንኩ ብድር እንዲያገኙ በማድረጋቸው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀናለ)፣ 33 እና 407 (2)ን በመተላለፋቸው፣ ያላግባብ በፈጸሙት ሥልጣን የመገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡ ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ ካላቸው ለመጠባበቅ ለጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

   

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

  መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ...

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...