Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናበመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

  በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩና የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ

  ቀን:

   ‹‹የምስክር ትንሽ ትልቅ የለውም›› አቶ በቀለ ገርባ

  የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው የሽብር ተግባር ወንጀልና ከባድ የማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን የተሰጠባቸው አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ በቀለ ገርባ፣ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ቀሩ፡፡

  ተከሳሾቹ አባልና አመራር የሆኑበትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) የፖለቲካ ድርጅት በሽፋንነት በመጠቀም፣ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስና በኃይል የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል በመሆን፣ ዓላማውን ለማሳካትና፣ በአገሪቱ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቅሶ ማስመስከሩ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ በሰጠው ብይን ሦስቱ ተከሳሾች በሽብርተኝነት አዋጁ አንቀጽ 3(3፣4፣ እና 6) ሥር የተደነገገውን ማለፋቸውን ማስረዳት መቻሉን ጠቁሞ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ የአቶ በቀለ ገርባን ግን ወደ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 257 (ሀ) በመቀየር በከባድ ማነሳሳት እንዲከላከሉ ብይን መስጠቱ ይታወሳል፡፡

  በመሆኑም ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክር እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔን አቶ አባዱላ ገመዳን፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳን፣ ምክትላቸውን ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ሌሎችንም በመከላከያነት ቆጥረው ነበር፡፡ ምስክሮቹ መጥሪያ እንዲደርሳቸውና የመከላከያ ምስክርነቱ ከማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንዲሰማም ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር፡፡

  ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከሳሾቹ የቀረቡ ቢሆንም፣ የመከላከያ ምስክሮች አልቀረቡም፡፡

  የእነ አቶ በቀለ ገርባ ጠበቃ አቶ አመሐ መኰንን ቀጠሮው ቀደም ብሎ የተሰጠ መሆኑን አስታውሰው፣ ለምን እንዳልቀረቡም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ መጥሪያው ወጪ እንዳልተደረገ ገልጾ፣ መመካከርና ማየት እንዳለበት በማስታወቅ ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡

  በዚህ መሀል አቶ በቀለ መናገር እንደሚፈልጉ አመልክተው ሲፈቀድላቸው፣ ‹‹በምስክሮች አቀራረብ ላይ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የምስክር ትንሽና ትልቅ የለውም፡፡ እኛ በእስር ቤት ዕቃ አይደለንም፡፡ መጥሪያ አልደረሰም ከተባለ መጻፍ ነው፤›› በማለት ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ በቀለ ለተናገሩት ምላሽ ሳይሰጥ ለኅዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...