Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊፀጉ ብርሃን ትሬዲንግ በሕገወጥ ብርበራ ተወሰዱብኝ ያላቸው ሰነዶች እንዲመለሱለት አመለከተ

  ፀጉ ብርሃን ትሬዲንግ በሕገወጥ ብርበራ ተወሰዱብኝ ያላቸው ሰነዶች እንዲመለሱለት አመለከተ

  ቀን:

  ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስተያየት እንዲሰጥበት ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል

  የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የወንጀል ምርመራ ቡድን ‹‹ደረሰኝ ሳይቆርጡ ሽያጭ ፈጽመዋል›› በሚል ጥርጣሬ ማስረጃ ለማሰባሰብ ከፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በመያዝ በፀጉ ብርሃን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ቢሮ ላይ ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረገው ብርበራ፣ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የወሰዳቸው ሠነዶች እንዲመለሱለትና በድርጊቱ ፈጻሚዎችም ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ድርጅቱ ለፍርድ ቤት ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. አመለከተ፡፡

  ፍርድ ቤቱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሰጠው የብርበራ ትዕዛዝ፣ የሚያዘው ነገር በሕገወጥነት የተጠረጠሩ ውሎችና ተያያዥ የሒሳብ ሰነዶች ላይ የተገደበ እንደሆነ፣ የሚበረበረው ክፍል ከወንጀሉ ጋር የተገናኘና ከተጠቀሰው ንብረት ውጪ መያዝ እንደሌለበት፣ የተያዘው ነገርም ታዛቢ ባለበት በዝርዝር መመዝገብ እንዳለበት አስቀምጧል፡፡

  አመልካች እንደሚለው ግን፣ ተጠሪው (የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን) የፍርድ ቤት የምርመራ ትዕዛዝ በመያዝ ኅዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አንድ የተጠሪ ሠራተኛና ሁለት የፖሊስ ባልደረባዎች በመያዝ ባካሄደው ብርበራ፣ ፍርድ ቤቱ ከሰጠው ትዕዛዝ ውጪ አመልካች ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ የሠራባቸው ከአርባ በላይ የሆኑ በርካታ ሰነዶች ተወስደውበታል፡፡ ሰነዶች ሲወሰዱም አልተመዘገቡም፡፡ ሰነዶች የተወሰዱትም ያለ ታዛቢ ነው፡፡ አሁንም ሰነዶች በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ እንዲሁም አመልካች በማመልከቻው ተጠሪ ታኅሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ለአመልካች በቀጥታ በጻፈው ደብዳቤ ለጉዳዩ አግባብነትና ተያያዥነት የሌላቸው ሰነዶች መወሰዳቸውንና አለመመዝገባቸውን ማረጋገጡን አስፍሯል፡፡

  ፍርድ ቤቱም ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ለቀረበበት አቤቱታ አስተያየቱን ይዞ የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አንደኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ አዟል፡፡

  ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጥር 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ለፀጉ ብርሃን ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ፣ የባለሥልጣኑ የኢንቨስቲጌሽን ኦዲት ዳይሬክቶሬት ድርጅቱ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ እያከናወነው ስላለው የንግድ እንቅስቃሴና የግብር ታክስ አከፋፈል አጣርቶ እንዲወስን አዟል፡፡

  ደብዳቤው ከተጻፈ በኋላ ባሉት ሦስት የሥራ ቀናት ውስጥ የመግቢያ ስብሰባ ለማድረግ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅና ስለድርጅቱ ሙሉ መረጃ መስጠት የሚችሉ የሥራ ኃላፊዎችን ይዞ ፕሮግራም እንዲይዝ፣ እንዲሁም ድርጅቱ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለውን የሒሳብ ሰነዶችና መዝገቦች ሃርድ ኮፒና ሶፍት ኮፒ በማቅረብ ሒሳባቸውን እንዲያስመረምሩ ሲል አሳስቧል፡፡

  ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በድርጅቱ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው አቶ ፀጉ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር ከአገር እንዳይወጡና የድርጅቱ ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ባለሥልጣኑ በፍርድ ቤት ያወጣው ዕግድ፣ በፍርድ ቤቱ ውድቅ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...