Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜና‹‹ለደቡብ ሱዳን ሰላም ያ ሁሉ ጥሪያችን ሳይሰማ ከንቱ ቀርቷል›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ...

  ‹‹ለደቡብ ሱዳን ሰላም ያ ሁሉ ጥሪያችን ሳይሰማ ከንቱ ቀርቷል›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

  ቀን:

  አዲስ አበባ ከየካቲት 24 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ሲደራደሩ የቆዩት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርና የቀድሞ ምክትላቸው ሪክ ማቻር፣ ሲጠበቅ የነበረውን ውይይታቸው ባለመስማማት ተጠናቀቀ፡፡

  ተደራዳሪዎቹ ያለውጤት ከተበተኑ በኋላ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባወጡት መግለጫ፣ በሁለቱ ወገኖች አለመግባባት የተነሳ በአገሪቱ ከዓመት በላይ በቆየው ቀውስ ‹‹ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ያሳዝናታል›› ሲሉም ተናግረዋል

  ኢጋድ በዚያች አገር ሰላም እንዲሰፈን ያደረገውን ያላሰለሰ ጥረት አንስተው፣ ይህ ጥረቱ ግን የተፈለገውን ውጤት አለማፍራቱን በመግለጫቸው ደጋግመው ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትርይለ ማርያም ሁለቱ ወገኖች ትርጉም አልባው ግጭት እንዲያበቃ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው፣ ከፖለቲካም ሆነ ከሞራል አንፃር ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

  በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የኢትዮጵያዝብና መላው የኢጋድ አካባቢ ከደቡብ ሱዳናውያን ጎን መሆናቸውን ያረጋገጡት አቶይለ ማርያም  በቅርብ ጊዜ ውስጥም ደቡብ ሱዳን ያጣችውን ሰላሟን እንደምታገኝ ተስፋቸውን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

  የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ)እስከ የካቲት 26 ቀን  ድረስ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችላቸውን ድርድር እንዲያጠናቅቁ ቀነ ገደብ አስቀምጦ እንደነበር ይታወሳል።

  በመጪው ሐምሌ ወር ሁለቱ ወገኖች የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የገቡትን ስምምነት እንዲያከብሩ ጥረቱ እንደሚቀጥልም፣ አቶይለ ማርያም በመግለጫቸው ላይ ጠቁመዋል።

   

   

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...