Sunday, August 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ከዋሽንግተን እስከ አዲስ አበባ ሥራ ፈጠራ ያገኛቸው

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  በአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት፣ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ ለሦስት ዓመታት በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ አማካይነት በግብርና መስኮች ላይ ሥራ መፍጠር የሚችሉትን በመመልመል ሲያሠለጥን ቆይቷል፡፡ ላለፉት ሁለት ዓመታት ቢዝነስን ከሐሳብ ወደ ተግባር በማሻገር ሥራና ገበያ ውስጥ መግባት የሚችሉበትን የቴክኒክ ሥልጠናና ድጋፍ ሲያገኙ የነበሩ 14 ሥራ ፈጣሪዎች ሐሳባቸውን ዕውን ማድረግ ይችላሉ ተብለው ዕውቅና ተሰጧቸዋል፡፡

  ፕሪሳይስ ኮንሰልት ኢንተርናሽናል አማካሪ ኩባንያ፣ በሰሊጥ፣ በማርና በወተት ምርቶች ላይ ለመሰማራት ሐሳቡና ፍላጎቱ የነበራቸውን ሰዎች በመቀበል አሠልጥኖ ያስመረቀው ሰኞ፣ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ነበር፡፡ ከአሜሪካ ባሻገር የአየርንድ መንግሥትም በተለይ በወተት ልማት ዘርፍ የሚሰማሩ ሥራ ፈጣሪዎችን በፋይናንስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

  በሰሊጥ፣ በወተትና በማር ምርቶች ላይ የሚሠራ ዘላቂ የአግሪ ቢዝነስ መፈልፈያ ፕሮጀክትን በመንድፍ እየተንቀሳቀሰ በሚገኘው ፕሪሳይስ ኮንሰልት አማካሪ ኩባንያ በኩል ድጋፍ አግኝተው ውጤታማ ከተባሉ ጀማሪዎች አንዱ አቶ ሳሙኤል ወልደሚካኤል ናቸው፡፡ የጂማን ተፈጥሮ ማር፣ በማቀነባበር ላይ የሚገኙት አቶ ሳሙኤል፣ የርኪሾ የማርና የሰም ንግድ ድርጅት ከመመሥረት አልፈው በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ጀርመን አገር ማር ለመላክ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል እንዳስታወቁት፣ ከ600 በላይ ገበሬዎችን ማር እንዲያንቡላቸው ሥልጠና በመስጠትና ቁሳቁሶችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ አቶ ሳሙኤል ለገበሬዎቹ የማር ቀፎና የማነቢያ ቁሳቁሶችን ከባንክ ብድር ወስደው ሲያቀርቡ፣ ገበሬዎቹ በምትኩ የቀፎውንና የሌሎች ማነቢያ ቁሳቁሶችን ዋጋ በማር ለውጠው ይመልሱላቸዋል፡፡

  በዚህ ዓመት አሥር ኮንቴይነር ወይም 200 ቶን ማር ወደ ጀርመን ለመላክ፣ ከጀርመን ኩባንያ ጋር ስምምነት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል ከሌሎች ጀማሪ የግብርና ዘርፍ ሥራ ፈጣሪዎች ልቀው በመገኘታቸው፣ ከአየርላዱ ምክትል ሚኒስትር ሻን ሼርሎክና ከአሜሪካዋ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ ዋንጫ ተቀብለዋል፡፡

  ሌላኛዋ ለየት ያለችው ጀማሪ የንግድ ሥራ ጀማሪ ደግሞ ኤቢሴ ባይሳ ናት፡፡ ኤቢሴ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪ ስትሆን፣ የተለያዩ የተፈጥሮ መዋቢያ ቅባቶችንና በተለያዩ መያዣ ዕቃዎች ውስጥ የሚዘጋጁ ሻማዎችን በዋሽንግተን ማምረት ጀምራለች፡፡ የምርቶቿን ናሙናዎችም በሥነ ሥርዓቱ ላይ አቅርባለች፡፡ ኤቢሴ ከኢትዮጵያ በምትረከበው ሰም፣ በእጅ የተመረቱ የተፈጥሮ ኮስሞቲክስና የመዋቢያ ቅባቶችን በማምረት አሜሪካ ውስጥ ገበያው እየደራላት መምጣቱን ለሪፖርተር ገልጻለች፡፡ ከማር ሰም ባሻገር ከቡና የሚጨመቁ የመዋቢያ ምርቶችም ታዘጋጃለች፡፡

  ሙሉ ለሙሉ ምርቶቿን ለገበያ ያቀረበችው ባለፈው ዓመት ሲሆን፣ በተለይ በአሜሪካ የግብርና ምርቶች መሸጫዎችና በተለያዩ የምግብ ሸቀጦች መሸጫ መደብሮች የተፈጥሮ ምርቶችን ለሚገዙ ደንበኞች ማቅረብ መጀመሯን ኤቢሴ ገልጻለች፡፡ ይህ ደግሞ በአሜሪካ በአሁኑ ወቅት ተፈላጊነቱ እየጨመረ የመረጣ የፍጆታ ዕቃዎች ገበያ ውስጥ የሚካተት መሆኑን ኤቢሴ ገልጻ፣ ከኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 500 ኪሎ ግራም የሰም ምርት ወደ አሜሪካ እያሰገባች ትገኛለች፡፡ በዚህ ዓመት ካለው የገበያ ፍላጎት በመነሳት የሰም ምርቱን በእጥፍ አሳድጋ ለመግዛት ሐሳብ እንዳላትና ወደ ፊት ኩባንያዋን ወደ ኢትዮጵያ ለማዛወር እንደምትፈልግ ትናገራለች፡፡

  ከዲሲ ወደ አዲስ አበባ ልትመጣ የቻለችውና ከፕሪሳይስ ኮንሰልት ኩባንያ ልትገናኝ የቻለችበትን አጋጣሚም አስረድታለች፡፡ በአሜሪካ የዳያስፖራ ፎረም ሲካሔድ፣ ዝግጅቱን የሚያሰናዳው የፕሪሳይስ አማካሪ እህት ኩባንያ ስብሰባ ላይ ገና ውጥን ላይ የነበረውን የንግድ ሐሳቧን ለታዳሚው አቅርባ እንደነበርና የማር ባለሙያ ከሆኑ የኩባንያው ባልደረባ ጋር በመነጋገር፣ ለንግድ ሐሳቧ መሳካት፣ ከኢትዮጵያ ማር አናቢዎች ጋር በማገናኘት የሰም ምርት አቅርቦት እንድታገኝ መንገዱን እንዳመቻቹላት ኤቢሴ ገልጻለች፡፡ አብዛኛውን የመዋቢያ ቅባቶች በእጇ በማምረት ላይ የምትገኘው ወጣቷ ሥራ ፈጣሪ፣ ምንም እንኳ እስካሁን ትርፍ ወደማምጣቱ ባትሻገርም፣ በዚህ ዓመት ትርፋማ የሚያደርጋት አቋም ላይ መሆኗን ገልጻለች፡፡ ከጋና ከምታገኛቸው ኮኮነት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ሰም በማቅለጥ፣ የኬምስትሪ ዕውቀቷን በመጠቀም ከኬሚካል ነፃ የተፈጥሮ መዋቢያና ሻማዎችን የምታመርተው ኤቢሴ፣  በእጅ የተሠሩ ማቀነባበሪያዎችን በመጠቀም ታመርታለች፡፡

  በፕሪሳይስ ኮንሰልት የሰስቴነብል አግሪቢዝነስ ኢንኩቤተር ፕሮጀክት ኃላፊ የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ከአሥራ አራቱ ሥራ ፈጣሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ፕሮጀክቱ ሲመጡ ሐሳብ ብቻ ይዘው መጥተዋል፡፡ ከተሰጣቸው ሥልጠና በኋላ መሠረታዊ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉን፣ ከአገር ውስጥ ባሻገር ወደ ውጭ አገር በመሄድ ልምድ እንዲቀስሙ መደረጉን ይጠቅሳሉ፡፡

  የአሜሪካው ተራድኦ ድርጅት በሰጠው ሁለት ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት፣ በአሁኑ ወቅት ከስምንት ሚሊዮን ዶላር በላይ በጀት ማግኘት እንደቻለ፣ ከዚህ ባሻገርም የአየርላንዱ ተራድኦ ተቋም፣ አይሪሽኤድ በሰጠው 500 ሺሕ ዶላር ለ18 የሥራ ፈጣሪዎች በወተት ማቀነባበር መስክ እንዲሰማሩ ለማስቻል ድጋፍ መስጠቱን አቶ አማኑኤል አስታውቀዋል፡፡

   

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች