ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሩዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና ምክትላቸው አቶ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ምስክሮቹ ያልቀረቡበት ምክንያት ሬጅስትራር ማዘዣ ወጪ ሳያደርግ በመቅረቱ እንደሆነ አስረድቶ አሁን ግን ማዘዣ ወጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
መከላከያ ምስክሮቹም ታህሳስ 17፣ 18 እና 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርበው እንዲሰሙ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡