Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትሩ ልብሳቸውን ቀይረው ኤርፖርት ሲሄዱ ባለሀብቱን ለመቀበል አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞችና ባለሀብቶች ተሰብስበው አገኙ፡፡ ከጋዜጠኛው ጋር እያወሩ ነው

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከፓርቲ ስብሰባ ቆይታ በኋላ ወደ ቢሯቸው ተመልሰው አማካሪያቸውን አስጠሩት]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ነህ አንተ?
  • ምንድነው ነገሩ?
  • ምንድነው ነገሩ ማለት?
  • ስብሰባ ብለው እኮ በጣም ረዥም ጊዜ ነው የቆዩት?
  • ሥራ አይደል እንዴ የያዝነው?
  • መቼም እንደዚህ ዓይነት ረዥም ስብሰባ ተሰብስባችሁ መፍትሔ ታመጣላችሁ ብዬ አስባለሁ፡፡
  • አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ መሆኗን ታውቃለህ?
  • ምን መስቀለኛ ብቻ በቋፍ ላይ ናት እንጂ?
  • ታዲያ ይህ መስመር መያዝ የለበትም ትላለህ?
  • ግን የእውነት መፍትሔ ለአገሪቷ አገኛችሁላት?
  • ለአገራችን ዕድገት ዋነኛዎቹን እንቅፋቶች አግኝተናቸዋል፡፡
  • ምን ይሆኑ?
  • ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ፀረ ልማት ኃይሎች፣ ሙሰኞች፣ ፀረ ሰላም ኃይሎች ናቸው፡፡
  • ስለዚህ በስብሰባው ላይ ተዋወቅኳቸው ነው የሚሉኝ?
  • እነማንን?
  • አቶ ኪራይ ሰብሳቢንና ወ/ሮ ሙስናን?
  • ምን እያልክ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ችግራችሁ እኮ ይኼ ነው፡፡
  • ምኑ?
  • ኪራይ ሰብሳቢንና ሙስናን እንደ ሌላ ግለሰብ ነው የምታወሩት፡፡
  • የምታወራው አልገባኝም፡፡
  • ሕዝቡ ምን እንደሚፈልግ ያውቃሉ?
  • ምንድነው የሚፈልገው?
  • እገሌ ሙሰኛ ነው እንድትሉ፡፡
  • ምን?
  • እገሌ ደግሞ ኪራይ ሰብሳቢ ነው እንድትሉ፡፡
  • እሱማ መቼ ይቀራል?
  • ክቡር ሚኒስትር አሁንም ለሕዝቡ ተረት ተረት ነው ይዛችሁ የመጣችሁት ማለት ነው?
  • የምን ተረት ተረት ነው?
  • ሕዝቡ የሚፈልገው ተረት ተረት ውስጥ ያሉትን ሙሰኛና ኪራይ ሰብሳቢዎች ነው፡፡
  • ምን ይዘባርቃል?
  • ሙሰኛውንና ኪራይ ሰብሳቢውን ሳያጋልጡ ሙስናንና ኪራይ ሰብሳቢነትን አጠፋለሁ ማለት ተረት ተረት ነው፡፡
  • ዋነኛው ኪራይ ሰብሳቢ አንተ እንደሆንክ እየተገነዘብኩ ነው፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ለአገሪቷ ችግሮች መፍትሔ ታመጣላችሁ ብዬ አስቤ ነበር፡፡
  • ከዚህ በላይ መፍትሔ ከየት አለ?
  • እናንተ በዛው በድሮ ያረጀ አካሄድ ላይ ናችሁ፡፡
  • ምኑ ነው ያረጀው አካሄድ?
  • በቃ የዛሬ 40 እና 50 ዓመት በፊት እንደነበረው ፕሮፖጋንዳችሁን ልትነፉ ነዋ፡፡
  • ምን ችግር አለው ፕሮፖጋንዳ መንፋት?
  • በፊት ሕዝቡ መረጃ የሚያገኘው ከመንግሥት ሚዲያ ብቻ ስለነበር ሊሠራ ይችላል፡፡
  • አሁን ለምን አይሠራም?
  • ክቡር ሚኒስትር ዘንግተውት ከሆነ 21ኛው ክፍለ ዘመን ከገባ ሁለት አሥርት ሊሆን ነው፡፡
  • አሁን ፕሮፓጋንዳ አይሠራም እያልክ ነው?
  • በዚህ ዘመን ሕዝቡ ሶሻል ሚዲያን ጨምሮ ከተለያዩ ቦታዎች መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡
  • ታዲያ ፕሮፓጋንዳችንን በሶሻል ሚዲያም ተጠቅመን ኪራይ ሰብሳቢዎችንና ሙሰኞችን እንመታቸዋለን፡፡
  • የአሁኑ ትውልድ የእናንተ ፕሮፓጋንዳ ሰልችቶታል፡፡
  • ታዲያ ምን እያልክ ነው?
  • የእናንተ አስተሳሰብ ያረጀና ያፈጀ ነው፡፡
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • መልቀቅ፡፡
  • ለማን?
  • ለወጣቱ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ለውጭ የሥራ ጉብኝት የመንግሥት ልዑክ ሆነው ሊሄዱ ስለሆነ የፋይናንስ ኃላፊውን አስጠሩት]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አሁን ጊዜ የለኝም፡፡
  • ምን ልርዳዎት ታዲያ?
  • ዶላር እፈልጋለሁ፡፡
  • የምን ዶላር ክቡር ሚኒስትር?
  • ጉዞ እንዳለኝ አታውቅም?
  • የምን ጉዞ?
  • ሜሞ አልደረሰህም?
  • የምን ሜሞ ክቡር ሚኒስትር?
  • ለአንድ ሳምንት የውጭ አገር የሥራ ጉብኝት አለብኝ ብዬ ልኬልሃለሁ እኮ፡፡
  • ለመሆኑ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈቃድ አግኝተዋል?
  • ከእሳቸው ጋር ነው የምሄደው፡፡
  • እንደዛ ከሆነ ጥሩ፡፡
  • ስለዚህ በአስቸኳይ ይዘጋጅልኝ፡፡
  • ምንድነው የሚፈልጉት?
  • አበል ነው የምፈልገው፡፡
  • ስንት ጊዜ ነው የሚቆዩት?
  • አንድ ሳምንት ነው፣ ግን የአንድ ሳምንት ብቻ እንዳትሠራለኝ፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • የምሄድበት አገር ነገሮች ውድ ናቸው፡፡
  • ቢሆኑስ ታዲያ ክቡር ሚኒስትር?
  • ስማ ውጭ ከሄድኩ እኮ ሰንብቻለሁ፡፡
  • አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር?
  • ሁሉም ሰው የሆነ ነገር እንዳመጣለት ይጠብቃል፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ለመሆኑ አንተ ውጭ አገር ሄደህ ታውቃለህ?
  • አላውቅም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አየህ ለዛ ነው የማይገባህ፡፡
  • ምኑ ነው ያልገባኝ?
  • ውጭ ስትሄድ ሞል ምናምን ስትገባ ብዙ ነገር ያምርሃል፡፡ በዛ ላይ እዚህ ሁሉም ሰው ዕቃ እንድታመጣለት ይጠብቅሃል፡፡
  • አሁን አላስፈላጊ የውጭ ጉዞዎች ለምን እንደተከለከሉ እየገባኝ ነው፡፡
  • ምን እያልክ ነው?
  • የሚሄዱት መንግሥትን ወክለው ለመነጋገር እንጂ ለሾፒንግ አይደለም፡፡
  • አንተን ማን ነው ተቆጣጣሪ ያደረገህ?
  • እኔንም ያስጠይቀኛል ብዬ ነው፡፡
  • ነገርኩህ እኮ አበሌን ጨመር አድርገህ ስጠኝ፡፡
  • ምን እያሉ ነው ታዲያ?
  • የሁለት ሳምንት አበል አዘጋጅልኝ፡፡
  • ኧረ ተው ክቡር ሚኒስትር?
  • ስማ የብር የመግዛት አቅሙ መቀነሱን እንዳትዘነጋ፡፡
  • ታዲያ እንዴት ነው የሁለት ሳምንት አበል የማዘጋጀው?
  • አንተ ባለፈው ፊልድ ለሳምንት ወጥተህ የሁለት ሳምንት አይደል የወሰድከው?
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • በቃ ለእኔም እንደዛው ስጠኝ፡፡
  • እሺ፡፡

  [የፋይናንስ ኃላፊው አበላቸውን ይዞ መጣ]

  • የስንት ጊዜ አደረግከው?
  • የሁለት ሳምንት፡፡
  • በጣም ጥሩ፡፡
  • ይኸው እንኩ፡፡
  • ምንድነው ይኼ?
  • አበልዎ ነዋ፡፡
  • ፊልድ አይደለም እኮ የምወጣው ውጭ አገር ነው የምሄደው?
  • አውቃለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ታዲያ በብር የምትሰጠኝ ለምንድነው?
  • እንዲቀይሩት ነዋ፡፡
  • የት ነው የምቀይረው?
  • ብላክ ማርኬት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ በአበላቸው ጉዳይ በጣም ተናደዋል፡፡ ቢሮ ተቀምጠው አንድ ባለሀብት ይደውልላቸዋል]

  • እንኳን ደስ አለዎት፡፡
  • ከዓመት በኋላ ውጭ ልትሄድ ነው ብለህ ነው እንኳን ደስ አለዎት ያልከኝ?
  • ውጭ ሊሄዱ ነው እንዴ?
  • ልሄድ ነበር ግን ለመቅረት እያሰብኩ ነው፡፡
  • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
  • አበሌን በብር ሰጥተውኝ ነዋ፡፡
  • ኪኪኪ…
  • ምን ያስቅሃል?
  • መንግሥት በጠኔ ተመቷል አይደል?
  • በምን ጠኔ?
  • በዶላር ነዋ፡፡
  • ለስሙ አንተም ልማታዊ ባለሀብት ነኝ እያልክ ታወራለህ?
  • እሱማ እውነት ነው፡፡
  • አንተ ግን የአገሪቷን ዶላር ትቦጠቡጣለህ እንጂ አንድ ዶላር አስገብተህ አታውቅም፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር የሚያዋጣኝን ቢዝነስ የማውቀው እኔ ነኝ፡፡
  • በጣም ያሳዝናል፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ብዙ መጨነቅ አያስፈልግዎትም፡፡
  • እንዴት አልጨነቅ?
  • በፊትም ቢሆን የመንግሥት ሥራ መቼ ለእርስዎ ገቢ አስገኝቶ ያውቃል? እኛው ባለሀብቶች አይደል እንዴ የምንደጉምዎት?
  • ይኼን ሁሉ ኔትወርክ በዚህ ሥራ ማግኘቴን አትዘንጋ፡፡
  • ያው ከመንግሥት ይልቅ ከእኛ የሚያገኙት ጥቅም ይሻላል ብዬ ነው፡፡
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • እና ክቡር ሚኒስትር ጉዞዎን ቢሰርዙት ይሻላል፡፡
  • ለምን?
  • አንድ ከባድ የሚመጣ እንግዳ አለ፡፡
  • ምን ዓይነት እንግዳ?
  • የእርስዎንም የዶላር ጥማት የሚያረካ እንግዳ፡፡
  • ማን ነው እሱ?
  • በቃ በቀላሉ ዶላር የሚያትም ሰው ማለት እችላለሁ፡፡
  • ሕገወጥ ዶላር?
  • አይደለም በጣም ሀብታም ሰው ነው ለማለት ነው፡፡
  • ጥሩ ነዋ፡፡
  • እንዲያው ሰሞኑን የሆነ ችግር ገጥሞት ነበር አሁን ግን ሁሉንም ነገር ጨርሶ ዛሬ ይገባል፡፡
  • ይኼን የመሰለ መረጃ አሁን ነው የምትነግረኝ?
  • መምጣቱን ለማረጋገጥ ሳጣራ ቆይቼ ነው፡፡
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • ኤርፖርት ሄደው አቀባበል ያድርጉለታ፡፡
  • በቃ ልብሴን ቀያይሬ ልምጣ፡፡
  • እሺ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ሌላ ምን ያስፈልጋል?
  • የአበባ ጉንጉን ነዋ፡፡

  [ክቡር ሚኒስትሩ ልብሳቸውን ቀይረው ኤርፖርት ሲሄዱ ባለሀብቱን ለመቀበል አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞችና ባለሀብቶች ተሰብስበው አገኙ፡፡ ከጋዜጠኛው ጋር እያወሩ ነው]

  • ብዙ ሰው ሊቀበላቸው መጥቷል አይደል እንዴ?
  • አዎን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ይኼ ሁሉ ሰው ግን እንዴት መጣ?
  • ባለሀብቱ እኮ ብዙ ወዳጆች አሏቸው፡፡
  • አንተም ወዳጃቸው ነህ?
  • እኔማ በዚሁ ለመወዳጀት አስቤ ነው፡፡
  • ይኼ ሁሉ ሰው እንደሚኖር አላወቅኩም ነበር፡፡
  • አብዛኛው ሰው እኮ ሊያስጨርስ ነው የሚመጣው፡፡
  • ምንድነው የሚያስጨርሰው?
  • የጀመሯቸውን ፕሮጀክቶች ነዋ፡፡
  • ያልከኝ አልገባኝም፡፡
  • እዛ ጋ ያለውን ባለሀብት አዩት?
  • አዎን፡፡
  • እሱ የጀመረውን ሕንፃ እንዲጨርሱለት ነው የመጣው፡፡
  • እሺ፡፡
  • እዛ ጋ ያለውን አርቲስት አዩት ደግሞ?
  • አዎን፡፡
  • እሱ ደግሞ የጀመረውን ቤት ሊያስጨርስ ነው የመጣው፡፡
  • አንተስ ምን ልታስጨርስ ነው?
  • ዕቁቤን!

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሚጠብቁት እንግዳ ከ30 ደቂቃ በላይ ቢጠብቁትም አልመጣም፣ በመካከል አንድ ሚኒስትር ደወሉላቸው]

  • የት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • አንድ ታላቅ ባለሀብት ለመቀበል ኤርፖርት ነኝ፡፡
  • ባይለፉ ጥሩ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን እያልከኝ ነው?
  • የሚጠብቁት ባለሀብት አይመጣም፡፡
  • ምን?
  • ባይሆን መንግሥት በቅርቡ እርስዎን ይቀበልዎታል፡፡
  • ምኑን ነው የሚቀበለኝ?
  • ቃልዎን!

   

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...

  ባንኮች እንዲዋሀዱ እስከ ማስገደድ ሊገባ እንደሚችል ብሔራዊ ባንክ ጠቆመ

  በአሁኑ ወቅት የባንኮች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ችግር የሚሆንና የውጭ...

  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተጀመረው የድርድር ሒደት አሳታፊ እንዲሆን ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት፣  በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...

  የኬንያ ምርጫ ቀጣናዊ አንድምታው

  በዘመናት ውስጥ ሳይናወጥ መዝለቅ የቻለ ይሉታል አንዳንዶች፡፡ የአገሮቹ መሪዎች...

  ባንኮች በትልልቅ ባለሀብቶችና በከተሞች ላይ ያተኮረ የብድር አቅርቦታቸውን እንዲያርሙ ብሔራዊ ባንክ አሳሰበ

  የአገሪቱ ባንኮች ዋነኛ ተግባራቸው የሆነው ብድር የማቅረብ አገልግሎት እንከን...

  ሰበበኞች!

  ዛሬ የምንጓዘው ከሜክሲኮ ወደ አየር ጤና ነው፡፡ ዛሬም፣ ነገም...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወዳጃቸው ከሆነ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ጋር ሻይ ቡና እያሉ በኬንያ ስለተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተጫወቱ ነው]

  ኬንያ በዚህ ደረጃ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ታደርጋለች ብዬ አላሰብኩም ነበር ክቡር ሚኒስትር። አዎ። ጥሩ ዝግጅት አድርገውበታል። ቢሆንም... ቢሆንም ምን ክቡር ሚኒስትር?  እባክህ ክቡር ሚኒስትር የምትለውን ነገር አቁም። ወዳጅ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አጥነት ችግሮችን የመፍታት ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም በዋና ጽሕፈት ቤቱ ሕንፃና ቢሮዎች ላይ ያደረገውን ዕድሳት መርቀው በመክፈት ጉብኝት እያደረጉ ነው]

  እጅግ ውብ ዕድሳት ያደረጋችሁት! በእውነቱ በጣም ድንቅ ነው፡፡ አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር። በጣም ድንቅ ነው። ዕድሳቱን ያከናወነው ድርጅት ጥሩ ልምድ ያለው ይመስላል? ተቋራጩ ማን እንደሆነ አልነገርኩዎትም እንዴ? የትኛው ተቋራጭ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ በስንዴ የተሸፈኑ ሰፋፊ እርሻዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገምገም ከስንዴ ምርት ድጋፍና ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ ጋር እየመከሩ ነው] 

  ክቡር ሚኒስትር እንደነገርክዎት በሁሉም ስንዴ አብቃይ አካባቢዎቻችን ያሉ አርሶ አደሮች ጥሪያችንን ተቀብለው መሬታቸውን በኩታ ገጠም አርሰው በስንዴ ዘር ሸፍነዋል። በጣም ጥሩ ዜና ነው። በጣም እንጂ። የሚገርምዎት...