Sunday, August 14, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊአስተዳደሩ የክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎችን የሥራ ዝርዝር እንዲያሳውቅ በፍርድ ቤት ታዘዘ

  አስተዳደሩ የክፍላተ ከተሞችና ወረዳዎችን የሥራ ዝርዝር እንዲያሳውቅ በፍርድ ቤት ታዘዘ

  ቀን:

  በከተማው የአፈጻጸም ችግር ጫፍ መድረሱ ተጠቁሟል

  ፍርድ ቤቶች የሚወስኗቸውን ቅጣትም ሆነ ሌሎች ውሳኔዎችን፣ በተለይ በተወሰኑ ክፍላተ ከተሞች ሥር የሚገኙ የወረዳ ኃላፊዎች ሊያስፈጽሙ ባለመቻላቸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የክፍላተ ከተሞችንና የወረዳዎችን የሥራ ድርሻ ዘርዝሮ እንዲልክ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደደረሰው ታወቀ፡፡

  በየክፍላተ ከተሞች ሥር የሚገኙ ወረዳዎችን በኃላፊነት እንዲመሩ የተሾሙ ኃላፊዎች፣ ፍርድ ያረፈባቸው ጉዳዮችን እንዲያስፈጽሙ ትዕዛዝ ሲደርሳቸው ‹‹ይኼ የኔ ድርሻ አይደለም፤›› በማለት አንዱ በአንዱ የሥራ ክፍል ወይም ድርሻ እያሳበበ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊከበር ባለመቻሉ፣ አስተዳደሩ የሥራ ድርሻዎቻቸውን ዘርዝሮ እንዲልክ መታዘዙን የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

  የሕግ የበላይነት እንዲከበርና በአጭር ጊዜና በተሻለ ወጪ የፍርድ አፈጻጸሞች እንዲተገበሩ ፍርድ ቤቶች እየሠሩ ቢሆንም አስፈጻሚ የወረዳ፣ የክፍላተ ከተሞችና የከተማው ኃላፊዎች እንቅፋት እየሆኑ ማስቸገራቸው ፍርድ ቤቶቹን እንዳማረረ ተገልጿል፡፡ በዚህም ኅብረተሰቡ ሳይንገላታና ሳይማረር መፈጸም ባግባቡ መወጣት እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ ቅሬታ ያቀርቡ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

  የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ የማይፈጸም ከሆነ ባለጉዳዮች ከመጉላላታቸውም በተጨማሪ፣ ላልተፈለገ ወጪና በመንግሥትና ፍርድ ቤቶች ላይ አመኔታ እንደሚያጡ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ይኼ ደግሞ ኢትዮጵያ በሕገ መንግሥቱ ያፀደቀቻቸውን ሕጎች በማስከበር ሒደት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያስከትል ስለሚችል፣ ሁሉም የከተማው አስፈጻሚዎች ትኩረት ሰጥተው ሊያስተውሉት የሚገባ ተግባር መሆኑን አክለዋል፡፡

  ፍርድ ቤቶች የሚያስተላልፉዋቸውን ትዕዛዞች ‹‹የሚመለከተው ሥራ አስፈጻሚውን ነው፤ የፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊውን ነው፣ ሥራ አስኪያጁን ነው ወዘተ›› በመባባል አላስፈላጊ መጓተትና ወጪ ከማስከተል በተጨማሪ፣ የመልካም አስተዳደር እጦትን በከፍተኛ ሁኔት የሚያመጣ በመሆኑ፣ በቀላሉ የሚታለፍ አለመሆኑን ለአስተዳደሩ የደረሰው ደብዳቤ እንደሚጠቁም ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በተለይ ከፍርድ ቤቶች የሚላኩ ትዕዛዞችን ተቀብሎ የሚያስፈጽም አካል ወይም የሥራ ድርሻ ያለው ኃላፊ፣ ማንነቱን ገልጾና ለይቶ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ የደረሰው አስተዳደሩ፣ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ በቀጥታ ከመፈጸም ይልቅ እሱም የደረሰውን ትዕዛዝ ወደ ክፍላተ ከተማ በማውረድ በእነሱ በኩል ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት ቢሞክርም፣ ተቀባይነት እንዳላገኝና ራሱ እንዲያቀርብ በድጋሚ መታዘዙን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

  ፍርድ ቤቶች ሕግን የመተርጎም እንጂ የማስፈጸም ሥልጣን እንደሌላቸው፣ ለፍትሕ መሳለጥና ለመልካም አስተዳደር መጎልበት አስፈጻሚዎች ወሳኝ ሚና ስላላቸው፣ አስፈጻሚው አካል አግባብ ባለው ሁኔታ መሥራት እንዳለበትም ምንጮች  አሳስበዋል፡፡

  የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ2007 በጀት ዓመት የሰባት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መድኅን ኪሮስ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ሲያቀርቡ፣ ፍርድ ቤቶችን ካጋጠሙአቸው ችግሮች አንዱ በአስተዳደሩ የሚደርስ የአፈጻጸም ችግር ነው፡፡ ከፍርድ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ፣ በተለይ የመሬት አስተዳዳር ለሚቀርብለት የአፈጻጸም ጥያቄ የተሟላ መረጃ አለመስጠት፣ መዘግየት፣ ባለድርሻ አካላት የፍርድ ቤት ትዕዛዝን አክብረው ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠት፣ በፍርድ አፈጻጸም ሒደት ፖሊስና የቀበሌ አስተዳደሮች ተገቢውን እገዛና ትብብር አለማድረግ፣ ወዘተ መሆናቸውን በዝርዝር ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...