Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማስገደል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አዲስ...

  የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማስገደል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አዲስ ክስ ቀረበባቸው

  ቀን:

  አራጣ ማበደርና ሌሎች የተለያዩ 39 የወንጀል ድርጊቶችን ፈጽመዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን የማስገደል ሙከራ ፈጽመዋል ተብለው አዲስ ክስ ቀረበባቸው፡፡

  በመዝገብ ቁጥር 203740/ ሰላሳ ዘጠኝ ክሶች ተመሥርቶባቸውና ዋስትና ተከልክለው በማረሚያ ቤት የሚገኙት አቶ ዓብይ አበራ፣ የግድያ ሙከራ አስደርገውባቸዋል የተባሉት ሦስቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧቸዋል፡፡

  አቶ ዓብይ የግድያ ሙከራውን ያቀነባበሩት ቀደም ብለው በተከሰሱባቸው የወንጀል ክሶች ተካተው አንድ ክስ የተመሠረተባቸው፣ በዋስትና በተለቀቁት አቶ መላኩ ሰለሞን አማካይነት መሆኑን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

  ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንደገለጸው አቶ ዓብይ በማረሚያ ቤት ሆነው ባስተላለፉት ትዕዛዝ መሠረት፣ ሦስቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የምስክርነት ቃላቸውን ሳይሰጡ ተራ በተራ ሊገደሉ እንደነበር የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

  በመጀመርያ ለሚገደሉት ምስክር 1,500,000 ብር መመደቡን፣ ከአቶ ዓብይ ጋር ክስ የቀረበባቸው አቶ ኢዮሲያስ አበራ ደግሞ የአንደኛውን ተገዳይ ምስክር አድራሻና ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን አጥንተው ማሳየታቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ገልጿል፡፡

  ለግድያ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን ገንዘብ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. እና በተለያዩ ጊዜያት በመከፋፈል በድምሩ 60,000 ብር የግድያ ትዕዛዝ ለተቀበለው ሰውና ጓደኛው   በመስጠት፣ ግድያው እንዲፈጸም መላካቸውን ዓቃቤ ሕግ ጠቁሟል፡፡

  ተከሳሾቹ ወንጀልን በሚመለከት ለፍትሕ አካላት ጥቆማ ወይም መረጃ የሰጠን ወይም በምስክርነት በቀረበ ሰው ላይ ጥቃት ለማድረስና ተፅዕኖ ለመፍጠር፣ ወይም ጉዳት ለማድረስ በሦስቱ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ላይ ድርጊቱን የፈጸሙ መሆናቸውን ዓቃቤ ሕግ አብራርቷል፡፡

  በመሆኑም ተከሳሾቹ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 (1ለ)፣ 27 (1) እና 39 (1ሀ) እና 444 (1) ሥር የተደነገገውን በመተላለፋቸው፣ በከባድ የሰው መግደል ሙከራና በጠቋሚዎችና በምስክሮች ላይ የሚፈጸም ወንጀሎች ክስ መመሥረቱን ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት አቅርቧል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...