Friday, August 19, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ባልትናየድንች ሽሮ (ለ3 ሰው)

  የድንች ሽሮ (ለ3 ሰው)

  ቀን:

  አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

  • 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) ተልጦ የተፈጨ ድንች
  • 1 መካከለኛ ጭልፋ (150 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
  • 1 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
  • ግማሽ የሻይ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
  • 3 የሾርባ ማንኪያ ዘይት
  • 1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
  • 1 የሻይ ማንኪያ ጨው

  አዘገጃጀት

  1. ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ ማቁላላት፤
  2. ትንሽ ውኃ ጠብ እያደረጉ በደንብ ማብሰል፤
  3. ዘይት ጨምሮ ሽንኩርቱ መብሰሉን ማረጋገጥ፤
  4. አዋዜ መጨመርና ማቁላላት፤
  5. ድንቹን መጨመር፤
  6. ርጥቡን ቅመም መጨመርና ጨው ማስተካከል፤
  7. መከለሻ ነስንሶ ወጡ እንደሽሮ ደረቅ ብሎ ሲንተከተክ አውጥቶ ቀዝቀዝ ሲል ለገበታ ማቅረብ፡፡

  ደብረ ወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) «የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት» (2003)

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ

  መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ...

  የፌደራሉ መንግሥት በትግራይ ኃይሎች ላይ ጥቃት አልፈጸምኩም አለ

  የጠቅላይ ሚንስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ...

  12ኛ ክልል እንዲቋቋም ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ ተወሰነ

  የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልል የመደራጀት አቤቱታን ተቀብሎ በመመርመር ሕዝበ...