Tuesday, August 16, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፓርትኦሊምፒክ ኮሚቴ የሪዮ ዲጀኔሮ ኦሊምፒክ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

  ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሪዮ ዲጀኔሮ ኦሊምፒክ ዕቅዱን ይፋ አደረገ

  ቀን:

  የብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ጥንቅር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ አገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2016 የሪዮ ዲጀኔሮ ኦሊምፒክ በአራት የስፖርት ዓይነቶች መሳተፍ የሚያስችላትን ዕቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀ፡፡

  ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው እንዳስታወቀው በመጪው የሪዮ ዲጀኔሮ ኦሊምፒክ ከአትሌቲክስ በተጨማሪ በብስክሌት፣ በወርልድ ቴኳንዶና በቦክስ ስፖርቶች አራት የወርቅ፣ አራት የብርና አራት የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን ለማስገኘት ዕቅድ ነድፎ እየሠራ ይገኛል፡፡

  የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያምን ጠቅሶ ይፋ የሆነው መግለጫ፣ ለዚህ ዕቅድ መሳካት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የድርጊት መርሐ ግብር እንደተሰጣቸው ገልጿል፡፡

  በአንድ የስፖርት ዓይነትና በውስን አትሌቶች ተንጠልጥሎ የቆየውን የአገሪቱን የኦሊምፒክ ተሳትፎ በሌሎች ስፖርቶች ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ ኦሊምፒክ ኮሚቴ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና በየደረጃው የሚገኙ አካላት ከወዲሁ የድርሻቸውን በመውሰድ ቅድመ ዝግጅት የጀመሩ መሆኑም አስታውቋል፡፡

  እ.ኤ.አ. በ2012 በተደረገው የለንደን ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ትኪ ገላና፣ በ10,000 እና በ5,000 ሜትር ሴቶች ጥሩነሽ ዲባባና መሠረት ደፋር አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፣ በወንዶች 10,000 ሜትር ደጀን ገብረመስቀል የብር፣ እንዲሁም በ5,000 ሜትር ሴቶች በሶፍያ አሰፋና በ5,000 ሜትር ወንዶች በታሪኩ በቀለ አማካይነት የነሐስ ሜዳሊያዎች ማግኘቷ ይታወሳል፡፡

   

  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ለሰላም ድርድሩ ‹‹ከአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት ውጭ ሌላው ተቀባይነት የለውም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

  የሰሜን ኢትዮጵያን ጦርነትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተጀመረው የአፍሪካ...

  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በንብረት ላይ የደረሰው የትራፊክ አደጋ በ494 በመቶ ጨምሯል

  በትራፊክ አደጋ 3,971 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል በአገር አቀፍ ደረጃ በተጠናቀቀው...

  አዲሱን የመንግሥት መዋቅር ዘርግተው ያጠናቀቁ ተቋማት 31 በመቶ ብቻ ናቸው

  በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ሥር ካሉት 160 የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ...

  ለተቃርኖ ምክንያት የሚሆኑ ከንቱ ድርጊቶች ይወገዱ!

  ሰሞኑን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት...