Thursday, August 18, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -

  ከ139 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ ነጋዴዎች ተከሰሱ

  - ማስታወቂያ -

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  ሐሰተኛ ማስረጃዎችን በማቅረብና የቡና ላኪነት ፈቃድ በማውጣት ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወደ ውጭ የሚላክ ቡና ገዝተው መላክ ሲገባቸው በመደበቅ ሳይልኩ በመቅረታቸው፣ መንግሥት ማግኘት የነበረበትን ከ139 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎች የካቲት 29 ቀን 209 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

  ክስ የተመሠረተባቸው ቡና ነጋዴዎች አብዱሰላም ጀማል፣ ኤልያስ ዘውዴ፣ አብዲ ሳሊህ፣ ጠሃ በየነ አህመድ (ያልተያዘ) እና ፉአድ ጀማል (ያልተያዘ) ሲሆኑ፣ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 1 (ሀ እና ለ)፣ 379 (1ሀ) ሥር ሕግ አንቀጽ 32 (1ሀ እና ለ)፣ 379 (1ሀ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ መንግሥታዊ ሰነዶችን አስመስለው በማዘጋጀትና በመጠቀም ሙስና መፈጸማቸውን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 18ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

  አብዱሰላምና ኤልያስ የተባሉት ተከሳሾች አብዲ በተባለው ተከሳሽ ስም የቡና ላኪነት ንግድ ፈቃድ ማውጣታቸውን ክሱ ያስረዳል፡፡ በስሙም የባንክ አካውንት ከፍተው 440,000 ብር በማስገባት አቅም ሳይኖራቸው እንዳላቸው በማስመሰል ለንግድ ሚኒስቴርና ለግብርና ሚኒስቴር ካሳዩ በኋላ፣ ወዲያውኑ ገንዘቡን ወጪ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ጠቁሟል፡፡

  ተከሳሾቹ ቡና እንደማያከማቹና እንደማያዘጋጁ እያወቁ ቡና ለማዘጋጀትና ለማከማቸት በሚል ከቡና ማከማቻና ማዘጋጃ ድርጅት ውል በመውሰድ፣ የብቃት ማረጋገጫም መውሰዳቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡ ሌሎች ለብቃት ማረጋገጫ የሚያስፈልጉ መሥፈርቶችን ለይስሙላ በማሟላት በንግድ ሚኒስቴር ዋና ምዝገባ ቅጽ ላይ ቡና የመላክና የውጭ ምንዛሪ የማስገኘት ዓላማ እንዳላቸው በመግለጽ በአብዲ ስም በወጣው ንግድ ፈቃድ የቡና ላኪነት ንግድ ፈቃድ በማውጣት፣ ለኤልያስ ውክልና የሰጡ በማስመሰል ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር አገናኝ ከሆነው ጃዊ ማንቡክ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር የቡና ግዥ ውል በመግባት 167.17 ቶን (1671.7 ኩንታል) ቡና ከገዙ በኋላ በመሰወር 709,500 ዶላር ወይም 13,757,205 ብር መንግሥት እንዲያጣ ማድረጋቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

  ተከሳሾቹ በተጨማሪም በተመሳሳይ መንገድ ግምቱ 538,479 ዶላር ወይም 10,826,495 ብር የሚያወጣ ቡና ገዝተው ወደ ውጭ ሳይልኩ በመቅረታቸው፣ መንግሥት የተጠቀሰውን የውጭ ምንዛሪ እንዲያጣ ማድረጋቸውንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አካቷል፡፡

  አብዱሰላም ካልተያዙት ጠሃ በየነና ፉአድ ጀማል ጋር በመሆን በተመሳሳይ መንገድ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ጋር አገናኝ ከሆነው ካስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር ውል በመግባት፣ 784.47 ቶን (7844.7 ኩንታል) ቡና ገዝተው ወደ ውጭ ሳይልኩ በመሸሸጋቸው መንግሥት 3,103,600 ዶላር ወይም 61,761,640 ብር እንዲያጣ ማድረጋቸውን የክስ ዝርዝሩ ይገልጻል፡፡

  እነዚሁ ተከሳሾች 674.17 ቶን (6741.7 ኩንታል) ቡና ገዝተው ሳይልኩ በመቅረታቸው፣ 2,619,566 ዶላር ወይም 52,677,507 ብር መንግሥትን ማሳጣታቸውን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

   

  በአጠቃላይ ተከሳሾቹ መንግሥት በድምሩ 6,971,145 ዶላር ወይም 139 023,247 ብር እንዳያገኝ ማድረጋቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

  ተከሳሾቹ የክስ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና ፖሊስ ያልተያዙትን አፈላልጎ ይዞ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ፣ ለመጋቢት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

   

  - Advertisement -spot_img

  የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

  - ማስታወቂያ -
  - ማስታወቂያ -spot_img

  በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች